1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሮን ጥቃት በመቀሌ ከተማ

ረቡዕ፣ መስከረም 4 2015

ዛሬ ጠዋት ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሰው አልባ ጢያራ (ድሮን) በተፈፀሙ ሁለት ተከታታይ ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 13 መቁሰላቸው ተዘገበ። መቐለ ሆስፒታል ከጥቃቱ በኋላ 5 የሞቱ ሰዎች መቀበሉን ገለልጿል። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ ከጥቃቱ በኋላ ሌሎች የሞቱ 5 ሰዎች እና 13 ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች መቀበሉን ዐስታውቋል።

 Äthiopien Luftangriff  in Mekele, Tigray
ምስል Million Haileselassie/DW

10 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 13 መቁሰላቸው ተገልጧል

This browser does not support the audio element.

ዛሬ ጠዋት ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሰው አልባ ጢያራ (ድሮን) በተፈፀሙ ሁለት ተከታታይ ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች 13 መቁሰላቸው ተዘገበ።  በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ዳግመ አምሳል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ጉዳቱ የደረሰው መጀመርያ ጠዋት 1 ሰዓት ከ40 ቀጥሎም 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ በተፈፀሙ ሁለት ጥቃቶች መሆኑም ተገልጧል። 

መቐለ ሆስፒታል ከጥቃቱ በኋላ 5 የሞቱ ሰዎች መቀበሉን ገለልጿል። ሌላው የህክምና ተቋም ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ ከጥቃቱ በኋላ ሌሎች የሞቱ 5 ሰዎች እና 13 ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች መቀበሉን የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረሥላሴ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በመጀመርያው ጥቃት (ጠዋት 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ በተፈፀመው ድብደባ) ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለመርዳታ በአካባቢው የሕክምና ድጋፍ እያደረገ የነበረ የሕክምና ባለሞያ እና ለቀረጻ ወደ ቦታው ተጉዞ የነበረ የካሜራ ባለሞያ ይገኙበታል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት፦ በዚህ ሳምንት ደረሱ የተባሉትን ከሰው አልባ ጢያራ የተሰነዘሩ የቦንብ ጥቃቶች በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን አስተያየት እንዳልሰጠባቸው ዘግቧል። 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW