1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«በምሥራቅ ጎጃም ዞን አንገሽ ቀበሌ 16 ሰዎች በድሮን ጥቃት ተገደሉ»

ማክሰኞ፣ የካቲት 18 2017

የካቲት13ቀን 2017ዓ.ም ረፋድ ላይ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ “አንገሽ” ቀበሌ በተፈፀመው የድሮን ጥቃት 16 ሠዎች መገደላቸውንና 11 መቁሰላቸውንም ነዋሪዎች አብራርተዋል።ሁለትና ሶስት የፋኖ ታጋዮች ወደ ከተማ መጥተው ካልሆን በስተቀር ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ ታጣቂዎቹ እንዳልነበሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

Ukraine-Krieg - Krieg der Drohnen | Kampfdrohne im Iran
ምስል፦ Iranian Army Office/Zuma/picture alliance

የድሮን ጥቃት በ“አንገሽ” ቀበሌ

This browser does not support the audio element.

ከአንድ ዓመት በላይ ያአስቆጠረውና እስካሁንም መሻሻል ያልታየበት የአማራ ክልል የሠላም እጦት አሁንም ለነዋሪዎቹ እንግልት፣ ጉስቁልና፣ ስቃይና ስጋት ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ጦርነቱን ተከትሎ በርካታ የድሮን ጥቃቶች ተፈፅመዋል፣ በርካቶችም ህይወታቸው አልፏል የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው ብዙዎች ናቸው።

“በጥቃቱ የተገደሉት “ንፁሐን ናቸው” የዓይን እማኞች

ሰሞኑነም በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ “አንገሽ” ቀበሌ በሱቆችና ሻይ ቤቶች ላይ ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት 16 ሠዎች መገደላቸውንና ከ10 በላይ መቁሰላቸውን አንድ የአይን እማኝ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው በሙሉ ንፁሐን ዜጎች ናቸው ብለዋል።

በድሮን ጥቃቶች በአማራ ክልል የሚገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው

“ጥቃቱ የተፈጸመው በሻይ ቤቶችና ሱቆች ላይ ነው” ነዋሪዎቹ

አስተያየት ሰጪው፣ በሰዓቱ ህፃናት ኳስ ሲጫወቱ እንደነበር ገልጠዋል። ከዚህ በፊት ቤቷ በመብረቅ ተመትቶባት ባለቤቷና አንድ ልጇን በሞት በአጣችና እንደገና በህብረተሰቡ ድጋፍ ሻይ ቤት በተሰራላት በአንዲት እናት ቤትና በሌሎች 3 ሱቆችና ሻይ ቤቶች ላይ የድሮን ጥቃቱ ደርሷል ብለዋል።

በአፋር ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

ምሥራቅ ጎጃም ዞን አማራ ክልል ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

በጥቃቱ 16 ሠዎች ስለመገደላቸው

የድሮን ጥቃቱ በመኖሪያ ቤቶችና በሻይ ቤቶች አካባቢ ህፃናት ኳስ በሚጫዎቱበት ቦታ እንደተጣለና ጉዳት እንደደረሰ ሌላ አስተያየት ሰጪ አመልክተዋል፣ “የፋኖ ታጣቂዎች ሻይ ቤትና ሱቅ ውስጥ ጉዳይ አልነበራቸውም፣ አልነበሩምም” ነው ያሉት። የካቲት 13ቀን 2017ዓ.ም. ረፋድ ላይ በተፈፀመው የድሮን ጥቃት 16 ሠዎች መገደላቸውንና 11 መቁሰላቸውንም በወቅቱ እንደተመለከቱ አብራርተዋል።ለእረፍትና ለህክምና ሁለትና ሶስት የፋኖ ታጋዮች ወደ ከተማ መጥተው ካልሆን በስተቀር ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ ታጣቂዎቹ እንዳልነበሩ ነው አስተያየት ሰጪዎች ያስረዱት።
ታጣቂዎቹ በአስፋልትና በከተማ ዳር ነው የሚንቀሳቀሱት እንጂ በጥቃቱ ቦታ አልነበሩም ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ።
በእለቱ አንድ የ15 ዓመት ታዳጊ እንደተገደላባቸው፣ ሌላው የ8 ዓመት ህፃን እንደቆሰላባቸው አንድ የአካባቢ ነዋሪ ነግረውናል።በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የተደረገ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ

“ጥቃቱ በታጣቂዎች ላይ እንጂ በንጹሐን ላይ ያነጣጠረ አልነበረም” የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ

የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ ጥቃቱ በእለቱ መፈፀሙን አምነው ሆኖም ዒላማ የነበረው “ጽንፈኛ” ብለው የጠሩት ኃይል እንደ ካምፕ ይገለገልበት በነበረ ትምህርት ቤትና በታጣቂው ኃይል ላይ ብቻ እንደሆነ ነው የገለፁት። በጥቃቱም 12 “ጽንፈኛ” ብለው የጠሯቸው አካላት እንደተገደሉ ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል፣ በአካባቢው የነበሩና የቡድኑ አባላት ይሁኑ ወይም አይሁኑ፣ ለአቅመ አዳም የደረሱ ይሁኑ ወይም አይሁኑ ያልታወቁ ሌሎች ሁለት ንፁሐንም ሳይገደሉ እንዳልቀረም ካአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ እንደደረሰአቸው ተናግረዋል።
 በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚጣሉ የድሮን ጥቃቶች በንፁሐን ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሆነ ቀደም ሲል የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ሲገልፁ ነበር፡፡
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW