1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድንበር አለመከፈት የፈጠረው ቅሬታ

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011

በሑመራ ኦምሓጀር እንዲሁም ራማ ዓዲኳላ በኩል ኢትዮጵያንና ኤርትራ የሚያገናኝ መንገድ አለመከፈቱ በአከባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ አስተያየታቸውን ለDW የሰጡ የድንበር አካባቢው ነዋሪዎች ከሌላው በተለየ ድንበሩ ባለመከፈቱ የህዝብ ለህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ግንኙነት እንዳናደርግ አግዶናል ይላሉ፡፡ 

Äthiopien und Eritrea Frieden Logo
ምስል DW/S. Fekade

የድንበር አለመከፈት የፈጠረው ቅሬታ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ማውረዳቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኙ መንገዶችን እና ድንበሮችን መክፈታቸው ይታወሳል። ሆኖም በሁመራ አካባቢ ያለው ድንበር እስካሁን አለመከፈቱ በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡  

በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ድንበሩ ያልተከፈተው የኤርትራ መንግስት ባለመፈቀዱ ነው ይላሉ፡፡ ውይይት ተደርጎ የድንበር መንገዱ በቅርቡ ይከፈታል ብለው እንደሚጠብቁም ይናገራሉ፡፡

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ድንበሩ እንዲከፈት ከመጀመርያው ጀምሮ ፍላጎት እንደነበር በመግለፅ እየተደረገ ባለው ንግግር በቀጣይነት ይከፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

በሑመራ ኦምሓጀር በኩል ያለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በተከዘ ወንዝ የሚለያይ ሲሆን፣ ቀደም ብሎ የተሰራ ድልድይ ሁለቱን ሀገራት ያገናኛል፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ተስፋለም ወልደየስ 

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW