የዶቼ ቬለዉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል
ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2016የዶቼ ቬለዉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል
ላለፉት አራት አስርተ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሞያ ያገለገለዉ የዶቼ ቬለዉ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል ረታ ከወጣ ቀናቶች ተቆጠሩ። ይልማ ኃይለሚካኤል በጀርመንዋ መዲና በርሊን ላይ ሲኖር ወደ 53 ዓመታትን አስቆጥሯል። በዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ቋንቋ ክፍል አገልግሎትን ጨምሮ በአሜሪካ ድምፅ ብሎም በሞስኮ ራድዮ በጋዜኝነት ብሎም የጋዜጠኝነት ስልጠና ሞያን በመስጠት አገልግልግሏል። አሁን ደግሞ በግሉ በጋዜጠኝነት ሞያዉ ያገኛቸዉን ልምዶች በስልጠና ብሎም በጽሑፍ ለመከተብ፤ በአዲስ የያዘዉን ብዕር ከወረቀት ጋር ለማገኛኘት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ባለፉት አስርተ ዓመታት የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ቋንቋ ክፍል አንዱ ምልክት የሆነዉ የበርሊኑ ወኪል በተቋሙ የመጨረሻዉን የጋዜጠኝነት ስራዉን ያጠናቀቀዉ፤ ባለፈዉ ማክሰኞ የፊታችን እሁድ በምስራቃዊ ጀርመን በሳክሶኒያ እና በቱሪንግ ክፍላተ ሃገራት ሊካሄድ እቅድ የተያዘለትን የአካባቢያዊ ምርጫን በተመለከተ በሰጠዉ ትንተና ነበር። የአጼ ኃይለሥላሴ መንግሥት ከመዉደቁ አራት ዓመታት ቀደም ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንጠናቆ ከአዲስ አበባ አዉሮፕላን ተሳፍሮ ወደ ምዕራባዊትዋ በርሊን ከተማ ሲገባ ቪዛ እንዳላስፈለገዉ ደጋግሞ ይልማ ይናገራል ። በርሊን የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጀምሮ በመከታተል ላይ ሳለ የአፄ ኃይለስላሴ መንግሥት ወደቀ ፤ በርሊን የገባሁት ጀርመንን በሁለት የከፈለዉ የበርሊኑ ግንብ በተገነባ በአስረኛ ዓመቱ ነዉ፤ ይኸዉ ግንብ በህዝብ ትግል ሲፈርስም፤ ምስራቅ በርሊን ለጉብኝ ሄጄ ሳለ ነዉ ሲል የጀርመን ቆይታዉን፤ የጋዜጠኝነት ሞያ ትዝታዎቹን በወፍ በረር እንዲህ አጫዉቶናል።
ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ