1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕ የመስፋፋት ፍላጎት እና ግብረ መልሱ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 17 2017

ፕሬዝዳንት ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን፣ ግሪንላንድንና የፓናማ ካናልን ወደአሜሪካ ግዛትነት የመጠቅለልን ሃሳብና ዛቻን እያንሸራሸሩ ነው። ይሄው ሃሳባቸው ከየሃገራቱ ተቃውሞና ግራ መጋባትን አስተናግዷል። የፖለቲካ ተንታኞች ይሄንኑ ቃላቸውን እንደ ጸብ አጫሪነት አልያም እንደ መደራደርያ መሳርያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

USA Gewählter Präsident Donald Trump
ምስል Evan Vucci/AP Photo/picture alliance

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጎረቤት ካናዳን ጨምሮ ሊጠቅልሉ የመፈለጋቸው አንድምታ

This browser does not support the audio element.

ፕሬዝዳንት ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን፣ ግሪንላንድንና የፓናማ ካናልን ወደአሜሪካ ግዛትነት የመጠቅለልን ሃሳብና ዛቻን እያንሸራሸሩ ነው። ይሄው ሃሳባቸው ከየሃገራቱ ተቃውሞና ግራ መጋባትን አስተናግዷል። የፖለቲካ ተንታኞች ይሄንኑ ቃላቸውን እንደ ጸብ አጫሪነት አልያም እንደ መደራደርያ መሳርያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንት ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ሰሞኑን የአሜሪካንን ግዛት የማስፋፋት ሃሳባቸውን ደጋግመው ሲገልጹ ነው የተደመጡት። ካናዳ፣ ፓናማ ካናል እና ግሪንላንድ የእስካሁን ኢላማቸው ሆነውዋል።

ይሄው ዛቻና ማስፈራርያ አሁን የተጀመረ አልነበርውም። በመጀመርያው የፕሬዝዳንትነታቸው ጊዜ ግሪንላንድን ከዴንማርክ ላይ ለመግዛት ሃሳብ አቅርበው ነበር። ይሄንኑ ሃሳባቸውን ዳግም እንዲንሰራራ ያደረጉት ደግሞ በዴንማርክ የአሜሪካ አምባሳደርን በሾሙበት እለት ነው። “ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት እና ለአለማቀፍ ነጻነት፣ አሜሪካ የግሪንላንድን ባለቤትነት ማረጋገጧ የማያወላዳ አስፈላጊ ነገር ነው” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ስለ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ምን አሉ? ቃለ መጠይቅ

የግሪንላንድ ጠ/ሚኒስትር ሚዩት ኤጅም ‘ግሪንላንድ የኛ ናት፣ ለሽያጭ አልቀረበችም፣ መቼም አትቀርብምም” በማለት መልስ ሰጥተዋል።  ግሪንላንድን የምታስተዳድረው የዴንማርክ ጠ/ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰንም “ግሪንላንድን ለሽያጭ አትቀርብም፣ ለጋራ ትብብር ሁሌም ክፍት ናት” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ብቻ አላበቁም። አትላንቲክና የፓስፊክን አለም የሚያገናኘው የፓናማ ካናል የመርከብ ክፍያ ካልተስተካከለ አሜሪካ ጠቅልላ ልትወስደው ትችላለች ብለው ዝተዋል። የፓናማ ፕሬዝዳንት ሆሴ ራውል ሙሊኖ የዶናልድ ትራምፕን ዛቻ ተቃውመው “እያንዳንዷ ስንዝር የካናሉ ቦታወች የፓናማ አካል ሆነው ይቀጥላሉ” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተመሠረቱ ክሶች ተነሱ

ዳግም ወደ ኋይት ሃውስ ለመግባት ቃለመሃላ ለሚፈጽሙባት እለት ጥቂት ቀናት የቀራቸው ዶናልድ ትራምፕ ቀልባቸውን የጣሉባት ሌላ ሃገር ጎረቤት ሃገር ካናዳ ናት። የካናዳውን ጠ/ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶን እንደ ሃገር መሪ ሳይሆን ልክ እንደ ሌሎቹ የአሜሪካ ግዛቶች ገዢ አድርገው የጠሯቸው ዶናልድ ትራምፕ ካናዳንም እንደ አንዷ የአሜሪካ ግዛት ማሰብ ጀምረዋል። “ብዙ ካናዳውያን ፣ ካናዳ የአሜሪካ ሃምሳ አንደኛ ግዛት እንድትሆን ይፈልጋሉ። ይሄ ደግሞ ግሩም ሃሳብ ነው” ብለዋል።

በርካታ ሃገራት በትራምፕ የስልጣን ዘመን ከአሜሪካ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ያስጨንቃቸዋል። የፖለቲካ ተንታኙ ኤሪክ ሃም የዶናልድ ትራምፕ የተስፋፊነት ሃሳብ የተንጸባረቀበት የሰሞኑ መልዕክት የሚያረጋጋ ሳይሆን የበለጠ ውጥረትን የሚያሰፋ ነው ብለዋል።ምስል Brian Snyder/REUTERS

 

በርካታ ሃገራት በትራምፕ የስልጣን ዘመን ከአሜሪካ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ያስጨንቃቸዋል። የፖለቲካ ተንታኙ ኤሪክ ሃም የዶናልድ ትራምፕ የተስፋፊነት ሃሳብ የተንጸባረቀበት የሰሞኑ መልዕክት የሚያረጋጋ ሳይሆን የበለጠ ውጥረትን የሚያሰፋ ነው ብለዋል። የፖለቲካ ፕሮፌሰሩ ክሪስቶፈር አዳምስ በበኩላቸው እንዲህ ያሉ መልዕክቶች በድርድር ላይ የበላይነት ለማግኘት የሚደረጉ አስቀድሞ የምጥቃት እርምጃወች ናቸው ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ሕገ ወጥ ባላቸው ስደተኞች ላይ የያዘው ዕቅድ

የነዚሁ የተጠቀሱት ሃገራት ዜጎች የዶናልድ ትራምፕ ህልምና ምኞት እውን የሚሆንበት ተጨባጭ መንገድ ለመኖሩ እርግጠኞች አይደሉም።

የዶናልድ ትራምፕ ቃል፤ እውነት ይሁን ሃሰት ለመገመት፣ ለመተንበይ አስቸጋሪ የሚሆንባቸው፣ የታሰበው ቀርቶ ያልታሰበው የተፈጸመባቸው ጊዜያት በርካታ ናቸው። አሁንም የዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ ግብ ለሚያይ፤ ለሚሰማው ግልጽ አይደለም። ባለፈው ሰኞ ግን ልጃቸው ኤሪክ ትራምፕ፣ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን፣ ግሪንላንድን እና ፓናማ ካናልን ከአማዞን ገበያ ሲገዙ የሚያሳይ የተቀናበረ ምስል በማህበራዊ ገጾቻቸው ላይ አጋርተዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደንና ተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነጩ ቤተ-መንግሥት ዉስጥ ተገናኙ

ይኸው ህልማቸው እንደወረደ በገሃዱ አለም ሲተገበር አይተን፣ ልክ አንደ ሉዚያና እና አላስካ ግዛቶች ግዢ ስማቸውን ታሪክ ላይ ያጽፉ ይሆን? ወይስ ይሄንን ዛቻ እንደማስፈራርያ ተጠቅመው ከየሃገራቱ የተሻለ የድርድር ውጤትን ያስመዘግባሉ? አሊያም እንደው ዝም ብለው አየሩን ሊሞሉ፣ ቀልብ ሊገዙ የተናገሩት ይሆን? በሂደት የሚታይ ይሆናል።

አበበ ፈለቀ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW