1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕ የባለሥልጣናት ምርጫ ስለመጪው አስተዳደራቸው ምን ይጠቁማል?

Eshete Bekele
ሰኞ፣ ኅዳር 2 2017

በአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪያቸው ካማላ ሐሪስን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ሥልጣን ይረከባሉ። እስካሁን ሦስት ተሿሚዎቻቸውን አሳውቀዋል። ባለጠጋው ኤለን ሙስክ እና አወዛጋቢው ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ ጁኒየር በትራምፕ አስተዳደር ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዶናልድ ትራምፕ የባለሥልጣናት ምርጫ ስለ አስተዳደራቸው ምን ይናገራል?

ዶናልድ ትራምፕ እና ኤለን ሙስክ
ባለጠጋው የኤክስ፣ የቴስላ እና የስፔስ ኤክስ ባለቤት ኤለን ሙስክ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።ምስል Anna Moneymaker/Getty Images

የዶናልድ ትራምፕ የባለሥልጣናት ምርጫ ስለመጪው አስተዳደራቸው ምን ይጠቁማል?

This browser does not support the audio element.

የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሱዚ ዋይልስ የመጀመሪያዋ የዋይት ሐውስ ሴት ቺፍ ኦፍ ስታፍ እንዲሆኑ መርጠዋል። የ67 ዓመቷ ዋይልስ የትራምፕን የምረጡኝ ዘመቻ በተባባሪ ሊቀ-መንበርነት የመሩ ሲሆን የዶይቼ ቬለ የአሜሪካ ዘጋቢ አበበ ፈለቀ እንደሚለው እንደተመራጩ ፕሬዝደንት “እዩኝ እዩኝ ማለት” የማይወዱ ናቸው። ሴትዬዋ በሪፐብሊካን ፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ ለረዥም ዓመታት ሠርተዋል። 

የዋይት ሐውስን የለት ተለት ሥራ በበላይነት የመምራት ኃላፊነት የሚኖራቸው ሱዚ ዋይልስ የተሰጣቸው ሹመት ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ “የተሳለጠ፣ ሥነ ሥርዓት ያለው መንግሥታዊ አመራር ተግባራዊ ለማድረግ ያለሙ ያስመስላቸዋል” ሲል አበበ ይናገራል።

 የአሜሪካ የምርጫ ውጤት እና የፕሪቶሪያው ስምምነት

የአሜሪካን ድንበር እንዲቆጣጠሩ ከዚህ ቀደም የፖሊስ መኮንን የነበሩት ቶም ሖማን ተመርጠዋል። ሖማን ከአራት ዓመታት በፊት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ላይ ሳሉ የአሜሪካ የፍልሰት እና የጉምሩክ አስፈጻሚ መሥሪያ ቤትን (ICE) በኃላፊነት የመሩ ናቸው።

“ስደተኞችን ዕቃችሁን ሸክፉ፣ ተዘጋጁ፣ እየመጣንላችሁ ነው” በማለት ሲያስፈራሩ የነበሩት ቶም ሖማን “በርካታ ስደተኞችን ያስጠጉ ከተሞች ላይ ዘመቻ እከፍታለሁ” ብለው ሲዝቱ እንደነበር አበበ ለዶይቼ ተናግሯል።

 ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።

የዶናልድ ትራምፕ ዋና ደጋፊ ኤሊስ ስቴፋኒክ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ ተመርጠዋል። ስቴፋኒክ በጎርጎሮሳዊው 2020 ጆ ባይደን ያሸነፉበትን ምርጫ ውጤት ለዶናልድ ትራምፕ ባላቸው ድጋፍ ለማጽደቅ አሻፈረኝ ብለው ነበር።  

የ67 ዓመቷ ሱዚ ዋይልስ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሐውስ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሆነው ተመርጠዋል።ምስል Andrew Harnik/AP Photo/picture alliance

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኒኪ ሔሊ እና የቀድሞው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ በአዲሱ አስተዳደር ውስጥ እንደማይሾሙ ትራምፕ አስታውቀዋል። ባለጠጋው የኤክስ፣ የቴስላ እና የስፔስ ኤክስ ባለቤት ኤለን ሙስክ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሙስክ የአሜሪካን መንግሥት የመከርከም ፍላጎት ያላቸው ይመስላል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የሮበርት ኬኔዲ የወንድም ልጅ ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ ትንሹ አወዛጋቢ ቢሆኑም ይሾማሉ ተብለው ሥማቸው ከሚጠቀስ መካከል ናቸው። ከኮቪድ 19 ክትባት ጋር በተያያዘ ያልተጨበጠ ወሬ በማናፈስ ይወነጀላሉ። ለመሆኑ የትራምፕ ምርጫ ስለመጪው አስተዳደራቸው ምን ይጠቁማል? 

በአሜሪካ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ አበበ ፈለቀ ማብራሪያ አለው። ማብራሪያውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ 

አበበ ፈለቀ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW