1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንን ከፍተኛ የክብር ኒሻን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 1 2009

የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ መንግስት ለሐገሪቱና ለሕዝቧ ሥልጣኔ፤ ብልፅግና፤ዕድገት እና አንድነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ 29 ታዋቂ ሰዎች ባለፈዉ ሳምንት የሐገሪቱን ታላቅ የኒሻን ሽልማት ሰጥቷል።

Asfa Wossen Asserate Unternehmensberater aus Frankfurt EINSCHRÄNKUNG
ምስል Gaby Gerster

የዶክተር አስፋወሰን መሸለም

This browser does not support the audio element.

 

የጀርመን ዳግም ዉሕደት 26ኛ ዓመት በተከበረበት ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ ሽልማቱን ከሐገሪቱ ፕሬዝደንት ከዮአኺም ጋዉክ እጅ ከተቀበሉት አንዱ ኢትዮጵያዊዉ የታሪክ ተመራማሪና ደራሲ ዶክተር ልጅ አስፋ ወሰን አስራተ ናቸዉ። በኒሻን አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ እንደተናገሩት፣ ዶክተር ልጅ አስፋዉ ወሰን አስራተ ለሽልማቱ የበቁት በአዉሮጳና በአፍሪቃ አህጉር መካከል ያለዉን ግንኙነት በሚገባ ተመልክተዉ ለሁለቱ ሕዝቦችና አህጉራት መቀራረብ ያበረከቱት አስተዋጽዖ ትልቅ በመሆኑ ነዉ። የዶክተር ልጅ አስፋወሰን ምክር እና ተሞክሮ በአሁኑ ሰዓት ትልቅ ስፍራ እንዳለዉ ፕሬዚዳንት ጋዉክ  አረጋግጠዋል። የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ከ ዶክተር ልጅ አስፋወሰን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ይቀርብበታል። የበርሊኑ ወኪላችን አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW