የዶይቼ ቬሌ የቀድሞ ዘጋቢ አስተያየት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የኤርትራዉን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ያመሰገነዉ ጎይቶም ፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ፈለግ በመከተል በኤርትራ ወህኒ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እስረኖችን ይፈታሉ ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል። የኤርትራን ሕዝብ በተለይም ደግሞ የአስመራን ነዋሪ በጥልቀት አቀዋለሁ የሚለው ጎይቶም፤ ኢትዮጵያ ዉስጥም በጋዜጠኝነት ረዘም ላሉ ዓመታት አገልግሏል። ጎይቶም ፤ የኢትዮጵያ ሠላም ማግኘት ለኤርትራም መረጋጋት መሠረት መሆኑን ተናግሮአል።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ