የጀርመኑ ፕሬዝዳት ሥልጣን መልቀቅ
ዓርብ፣ የካቲት 9 2004ማስታወቂያ
የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የፖለቲካ ተባባሪዎቻቸዉ ዛሬ ሥልጣናቸዉን የለቀቁትን ፕሬዝዳት ክርስቲያን ቩልፍን የሚተካ ፖለቲከኛ እያፈላለጉ ነዉ።የዛሬ ሁለት አመት ግድም በሜርክል ምርጫና ጠንካራ ድጋፍ የፕሬዝዳትነቱን መንበር የያዙት ቩልፍ በሙስና እና ጋዜጠኛን በማስፈራራት ጥፋት ክፉኛ ሲወቀሱና ሲተቹ ነበር።ጀርመን ፕሬዝዳንቷ ሥልጣን ለመልቀቅ ሲገደድባት ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ቩልፍ ሁለተኛዉ ናቸዉ።ቩልፍ ተክተዋቸዉ የነበሩት ሆርስት ከለር ሥልጣን ለመልቀቅ የተገደዱት አፍቃኒስታን ሥለሠፈረዉ የጀርመን ጦር ተልዕኮ በሰጡት አስተያየት ሰበብ ነበር።ሥለ ቩልፍ ሥንብትና ማንነት የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጭር ዘገባ አለዉ።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ