1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች የፀደቀበት 75ኛ ዓመት

ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2016

"የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ አይደለም" ይላል በጀርመን የዛሬ 75 ዓመት የፀደቀዉ እና ተግባራዊ የሚደረገዉ የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት - ሕገ መንግሥት አንቀጽ አንድ። ጀርመን ሕገ መንግሥት የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት የዛሬ 75 ዓመት ፤ በጎርጎረሳዉያኑ 1949 ዓ.ም ተደነገገ። በዚህ እለት የጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክም ተመሰረተ።

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት - በበርሊን
የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት - በበርሊንምስል Karl-Heinz Sprembe/picture alliance

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች 75ኛ ዓመት፦ "የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ አይደለም"

This browser does not support the audio element.

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች 75ኛ ዓመት፦ "የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር  የሚነካ አይደለም"

"የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ የሚደፈር አይደለም" ይላል በጀርመን የዛሬ 75 ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ የፀደቀዉ እና ተግባራዊ የሚደረገዉ የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት ማለትም ሕገ መንግሥት አንቀጽ አንድ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ሰነበታችሁ።

"የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ የሚደፈር አይደለም" ሲል ከአንቀፅ አንድ የሚጀምረዉ የጀርመን መሰረታዊ ህግጋት  ማለትም የጀርመን ሕገ መንግሥት ተግባራዊ መሆን የጀመረዉ የዛሬ 75 ዓመት በዛሬዋ እለት በጎርጎረሳዉያኑ 1949 ዓ.ም ነበር። በዚሁ እለትም የጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክ ተመሰረተ።

ጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት፤ አንቀጽ አንድ ላይ ጎልቶ የተቀመጠዉ "የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ የሚደፈር አይደለም" የሚለዉ አርፍተነገር፤ የጀርመን ብሔራዊ ሶሻሊስት የናዚ አስተዳደር በሰዉ ልጅ ላይ አቻ የማይገኝለት ከፍተኛ ግፍ እና ዉድመት ከፈፀመ በኋላ በተፈጠረዉ የጥፋተኝነት ስሜት የተፃፈዉ። ይህም የጀርመን ናዚ ከጎርጎረሳዉያኑ 1939 እስከ 1945 በተካሄደዉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነትና በመላው አውሮጳ ለተገደሉ ስድስት ሚልዮን አይሁዳዉያን ተጠያቂ ነበር ።

በጀርመን ሕገ መንግሥት እማረካለሁ፤ የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት በፀደቀበት ዓመት ፤ እኔም ተወለድኩ በመሆኑ ሁለታችንም 75ኛ ዓመታችንን ይዘናል ያሉን በጀርመን የአፍሪቃ እና የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪ፤ የታሪክ ምሁር ብሎም  በጀርመን ታዋቂ ደራሲ የሆኑት ልዑል ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ ናቸዉ።

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር -በበርሊን መሰረታዊ ሕግጋቶች የፀደቀበት 75ኛ ዓመት ሲከበርምስል Michael Kappeler/dpa/picture alliance

«ጀርመንአንድ  ሺ ባለዉ የጀርመን ታሪክ ዉስጥ  ከፍተኛ ቦታን ይዛ የተቀመጠችዉ እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር 1949 ዓም የተጻፈዉ አዲስሁ የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት ማለትም የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት ነዉ። በዚህ በጀርመን ሃገር የሚገኝ ማንኛዉም ተመራማሪ እንዲሁም የታሪክ ምሁር  ያዉቃል። ጀርመን እንዲህ ብዙ ሕዝብ የተሳተፈበት ሕገ መንግሥት በአንድ ሺህ ታሪኳ ኖርዋት አያዉቅም።»

መሰረታዊ ህግጋት መጽደቅ

የጀርመን መሰረታዊ ህግጋት በፀደቀ እለት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምዕራባውያን ድል አድራጊ ኃይሎች ከሆኑት በዩናይትድ ስቴትስ ፣ ታላቋ ብሪታንያና በፈረንሳይ ቁጥጥር  ስር ከሚገኙት የጀርመን ግዛት ቀጣናዎች የጀርመን ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ተመሰረተ። በሶቭየት ህብረት ቁጥጥር ስር የነበረዉ የጀርመን የምስራቁ ክልል እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 1949 ዓ.ም የጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (GDR) ሆነ ተቋቋመ።  የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ባበቃ በሦስተኛ ዓመት የወጣዉ እና ዛሬ 75ኛ ዓመት የሞላዉ የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት እንዴት እና በነማን ረቀቀ ይሆን?

ሕገመንግሥት ካረቀቁት መካከል የቀድሞ ጊዜ የጀርመን ፓርላማ አባላትሴቶችም ይገኙበታል ምስል Erna Wagner-Hehmke/Haus der Geschichte/dpa/picture alliance

«በዝያን ጊዜ ይህን ህግጋት እንዲወጣ የሕግ አዉጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ ነበር። በወቅቱ ጀርመንን ተቆጣጥረዉ ያስተዳድሩ የነበሩት አራቱ ኃያላን ሃገሮች፤ ሶቭየት ህብረት የተቆጣጠረችዉ ምስራቃዊ የጀርመን ክፍል ሲቀር ሦስቱ ኃያላን ሃገራት፤ ማለትም የተባበሩት የአማሪካ፤ የታላቅዋ ብሪታንያ እና የፈረንሳይ መንግሥታት ተስማምተዉ የሕግ አዉጭ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደረገ።  በዝያን ወቅት ጀርመን ያልዋት ትላልቅ ምሁራን እንዲሁም የናዚ ተቃዋሚዎች ተሰብስበዉ፤ ለብዙ ወራቶች ከተማከሩ በኋላ  በጀርመንኛዉ "  Grundgesetz"  የተባለዉን ማለትም "የጀርመን መሰረታዊ ህግጋት ስምምነት"  የተባለዉን አዉጥተዉ አፀደቁ። የዚህ መሰረታዊ ሕግ ሃሳብ እዉነተኛዉ ሁሉን አቀፍ የሆነ ሕገ መንግሥት ከተቀላቀሉ በኋላ ነዉ የሚደረገዉ ተብሎ ስሙን  ሕገ መንግሥት ሳይሆን - መሰረታዊ ህግጋት ብለዉ ያወጡበት ምክንያት ለዚህ ነዉ። ቆየት ብሎ ሁለቱ ጀርመኖች በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓም ሲቀላቀሉ እና አንድ ሲሆኑ፤ በሚያስገርም ሁኔታ ምስራቅ ጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች የሚለዉን ተቀይብያለሁ ስትል በመግለፅዋ አዲስ ሕh, መንግሥት ማምጣት አላስፈለገም።     

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋት - በበርሊንምስል Maja Hitij/Getty Images

በምሥራቅ ጀርመን ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁት እና በጀርመን በምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያነት የሚያገለግሉት ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ በ 2021 ከጀርመን ፕሬዚደንትን የክብር ኒሻን ያገኙ ናቸዉ። የጀርመን መሰረታዊ ህግ በቅድምያ የሰብዓዊ መብት እንዳይነካ ፤ የሰዉ ልጅ ነጻነት እንዲጠበቀ፤ የደነገ እና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሉ ያስረዳሉ።

"የሰዉ ልጅ ስብዕና እና ክብር የሚነካ የሚደፈር አይደለም" ይህ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ የሚስማማበት ይመስለናል።   ልዑል ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ እና ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ ለሰጡን ቃለ ምልልስ እበዶቼ ቬለ ስም እያመሰገንን ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW