1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ምርጫና አፍሪቃ

እሑድ፣ መስከረም 12 2006

ጀርመን የፌደራል ምክር ቤት ምርጫ ሲካሄድ ዋለ። ዜጎች ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ በየምርጫ ጣብያዉ ድምፃቸዉን ሲሰጡ ነዉ የዋሉት። አዲሱን ምክር ቤት ለመምረጥ ጥሪ የተደረገላቸዉ ዜጎች 62 ሚሊዮን ግድም ሲሆኑ፤ ከነዚህ መካከል ሶስት ሚሊዮኑ ለመጀመርያ ግዜ ጽምፅ የሚሰጡ ናቸዉ።

German Chancellor and leader of Christian Democratic Union (CDU) Angela Merkel waves as she arrives to address supporters after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) at the CDU party headquarters in Berlin September 22, 2013. Merkel's conservatives won the most votes in a German election on Sunday, putting her on track for a third term, but it was unclear whether she would be able to preserve her centre-right coalition or be forced to work with her leftist rivals, an exit poll showed. At right is CDU party secretary general Hermann Groehe, and at left is Thomas Strobl, leader of the Christian Democratic Union (CDU) in Baden-Wuerttemberg . REUTERS/Kai Pfaffenbach (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል Reuters

የቅርብ ዝንባሌ መለክያ መጠይቅ እንዳመለከተዉ፤ በስልጣን ላይ ያሉት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፤ ለቀጣይ አራት ዓመት የስልጣን ዘመን ተስፋ ሊያደርጉ ይችላሉ። ሆኖም ግን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሚመሩት የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ(CDU) ስልጣኑን መልሶ ለማረጋገጥ ከየትኛዉ ፓርቲ ጋር ጥምር እንደሚሆን የታወቀ ነገር የለም።

እስካሁን በምክር ቤቱ ተወክለዉ ከቆዩት ፓርቲዎች መካከል ምናልባትም ከ 5 በመቶ ዉጤት በታች ድምፅን በማግኘት በምክር ቤት ያለመግባት አደጋ ያለበት ለዘብተኛ አቋም ያለዉ FDP ፓርቲ መሆኑ ተነግሮአል። የምርጫዉ የመጀመርያ ዉጤት ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። የምርጫዉ አጠቃላይ ዉጤት እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቆ ይፋ ይሆናል።


በምርጫ ሥልጣን የሚይዘዉ መንግስት ለሀገሪቱ ይሻላል የሚለዉን አዲስ የፖለቲካ መርህ ሲቀይስ፤ ጀርመን ስለ አፍሪቃ የምትከተለዉም መርህ በአዲስ ምዕራፍ ይቀጥላል። የአፍሪቃን ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ድርጅቶች፤ በጀርመን አዲስ ከሚመረጠዉ መንግስት ምን ተስፋ ያደርጋሉ? በአፍሪቃ ዉስጥ ለሚንቀሳቀሱ የጀርመን ድርጅቶች፤ ይበልጥ አክብሮት፤ አዳዲስ ሃሳቦች፤ ድጋፍና ዋስትና እንደሚያስፈልግ አብዛኞች ይናገራሉ። የዶቼ ቬለዋ ሽቴፈኒ ዱክ ሽታይን እንደዘገበችዉ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ቃል ተገብቶ ነበር ።
ለዘብተኛ አቋም ያለዉ ፓርቲ የ FDP አባል የሆኑት፤ የጀርመኑ የልማት ተራድኦ ሚንስትር ዲርክ ኔብል በጎ,አ 2010 ዓ,ም የሚስትርነት ሥልጣንን በያዙ ስድስት ወር ባልሞላ ግዜ ዉስጥ ጥር ወር መጀመርያ፤ አፍሪቃን ጉብኝተዉ ሲመለሱ፤ ሁኔታዉ ቀላል ባይሆንም ጥሩ ነገር ለመሥራት ፍላጎታቸዉን አሳይተዉ ነበር፤
«በአፍሪቃ ለእድገት የሚያስችል እጅግ ግዙፍ እቅም እንዳላት ግን በዚያዉ መጠን ከባድ ችግር መኖሩን ተረድቻለሁ። ለእድገት የሚሆን ግዙፍ አቅም እና እጅግ ብዙ ችግር ደግሞ ከፍተኛ ጥረት እና ጉልበት ይጠይቃል። ስለዚህም የጀርመን ፊደራል ሊፐብሊክ የልማት የትብብር ዋና ትኩረቱን በጎራባች አህጉር አፍሪቃ ላይ ቢያደርግ ትክክል ነዉ»

ምስል DW/M. Gopalakrishnan

የእስከ ዛሪዉ ጥረት ምን ዉጤት አስገኘ? ዋና መቀመጫዉን በበርሊን ያደረገዉ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት «አፍሪቃ አቪኒር » ዋና ተጠሪ እንደ ኒኮላይ ሮሸርት ከአህጉሪቱ ጋር ለመቀራረብ እና አጥጋቢ ሥራን ለመተግበር ብዙ መሰራት ያለበት ነገር አለ ። የልማት ድርጅቶች ስለ አፍሪቃ ፖለቲካ ሥልጠናን ይሰጣሉ። የጀርመን መንግስትም ወደፊት ይህንን ማድረግ ይጠበቅበታል ባይ ናቸዉ። ተግባራዊ መደረግ አለባቸዉ ከሚባሉት ዝርዝር ነገሮች በአንደኝነት፤ ከአፍሪቃዉያኑ አጋሮቻችን ጋር በእኩል ደረጃ የምንወያይበት መድረክ መኖር ይኖርበታል፤
«አፍሪቃዉያኑ በመካከላችን የሚደረገዉ ዉይይት እና አቀባበል እንዲቀየር እንደሚፈልጉ ማወቅ አለብን። ከአፍሪቃዉያኑ ጋር የሚደረገዉ ዉይይት በእኩል አይን እንዲሆን የኛ ድርጅት «አፍሪቃ አቪኒር» ብቻ ማድረግ አይችልም። ገንዘብ የምናገኘዉ ከ BMZ ማለትም የጀርመን የኤኮኖሚና የልማት ትብብር ሚኒስቴር በመሆኑ ለሌላ ተግባር ማዋል አንችልም። ለምሳሌ ከአፍሪቃ ሰዎችን መጋበዝ አንችልም። ለዚህም ነዉ፤ ከማን ጋር ነዉ ደረጃዉን በጠበቀ እኩል በሆነ ሁኔታ ዉይይት ማካሄድ የሚቻለዉ ብለን የምጠይቀዉ»

እንደ ሮይሸርት በሚኒስቴር ደረጃ ጀርመን የሚመጣ አንድ አፍሪቃዊ ባለስልጣን፤ ከጀርመኑ እኩል አይታይም። በሚንስትርነት ደረጃ አቀባበል የሚደረግለት አፍሪቃዊ ባለስልጣን፤ እጅግ ጥቂት በመሆኑ ለአፍሪቃዉያኑ አልተስማም ሲሉ በበርሊን «አፍሪቃ አቪኒር» የተሰኘዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ድርጅት ዋና ተጠሪ ሮሸርት ይገልጻሉ። በቀድሞዉ የጀርመን መራሄ መንግስት፤ በጌሃርድ ሽሮደር ሥልጣን ዘመን የአፍሪቃ የቡድን ስምንት ተጠሪ የነበሩትና፤ አሁን በአፍሪቃ ላይ ጥናት የሚያደርገዉ ተቋም ምክትል ተጠሪ፤ ኡሺ አይድም በዚህ ጉዳይ ይስማማሉ፤
«አፍሪቃ እንደ አንድ አጋር በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ትክክለኛ ማዕረግን እና ክብርን አላገኘችም። የጀርመን የዉጭ ጉዳይ መርሕ፤ በደቡብ ክፍል ለሚገኙት የጀርመን አጎራባች ሀገሮች ትኩረት እንዲሰጥ አደርግ ነበር። የጋራ ችግራችንን በማወቅ እና ያለዉን ችግር በመተባበር እንዲት መፍታት እንደምችል በጋራ እንሰራ ነበር»

የጀርመንን ኤኮኖሚ በተመለከተ ከአፍሪቃዉያኑ አጋሮች ጋር ያለዉ ትብብር የሚያስወቅስ አይደለም። ጎረቤት አህጉር አፍሪቃ ላይ አንድ ነገር ለመሥራት የሚሞክሩ የጀርመን ባለንዋዮች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ ጨምሮአል። በጋና በሴኔጋል እንዲሁም በናይጀርያ ለረጅም ዓመታት የሰሩት የጀርመን ካቶሊክ የርዳታ ማህበር ፤ማርቲን ቪልደ ስላላቸዉ ተሞክሮ ይገልጻሉ።«ከሁሉም በላይ፤ መካከለኛ መጠን ማዋለ ንዋይ አፍሳሱች ትኩረት ሊሰጠን ይገባል። አንድ እጅግ ግዙፍ የሆነ ድርጅት፤ አፍሪቃ ሥራ መስራት ቢፈልግ ድጋፍ አያስፈልገዉም። አነስተኛ መዋለ ንዋይ ይዘዉ የሚሄዱ እና ሀገራትን ቀስ በቀስ መለማመድ ያለባቸዉ ምንም ዋስትና የሌላቸዉ ድርጅቶች፤ በአፍሪቃ ቀላል ሁኔታ አይጠብቃቸዉም። እጅግ ከፍተኛ ችግር ነዉ።»ቪልድ በአፍሪቃ የሚንቀሳቀስ የጀርመን ድርጅት በጀርመን ኤኮነሚ መደገፍ አለበት ይላሉ። በተለይ በአፍሪቃ አነስተኛ መዋዕለ ንዋይ ይዘዉ የሚሄዱ የጀርመን ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል። ይህ ደግሞ ርዳታ ብቻ ሳይሆን በአፍሪቃ ከሌሎች ተፎካካሪ መዋለ ንዋይ አፍሳሾች ጋር ለዉድድር መቅርብ እንዲያስችላቸዉ መሆን ይኖርበታል።

ምስል picture-alliance/dpa

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW