የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 1 2013ማስታወቂያ
ጀርመን በዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) በኩል ለኢትዮጵያ የ8.5 ሚሊዮን ዩሮ ሠብአዊ ርዳታ ሠጠች።ዓለም አቀፉ ድርጅት እንዳስታወቀዉ ጀርመን የሰጠችዉ ርዳታ ኢትዮጵያ ዉስጥ በግጭትና በዓየር ንብረት ለዉጥ ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት መርጃ የሚዉል ነዉ።በኢትዮጵያ የWFP የሕዝብ ግንኙነት እንዳለዉ ርዳታዉ በተለይ በሶማሌ ክልል በዓየር ንብረት ለውጥ መዛባት ፣ በትግራይ ደግሞ በግጭት ለተጎዱ ሰዎች ምግብ ለመርዳት የሚደረገዉን ጥረት ያግዛል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ