1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን ቅኝ ገዢ ኃይል ወደ ናሚቢያ እግሩን ያስገባበት አጋጣሚ

ሰኞ፣ መጋቢት 9 2016

በጎርጎርሳውያኑ 1880ዎቹ አውሮጳውያን የካርታ ስራ ባለሞያዎች 2 ሺ ኪሎሜትሮችን በሚያካልለው የባህር ሰርጥ አካባቢ በወቅቱ ለመርከብ ማቆሚያነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሶስት አስተማማኝ አካባቢዎችን መለየት ችለው ነበር። ነገር ግን ተጓዞች ከመርከብ ሲወርዱ 140 ኪ/ሜ የሚረዝም ናሚብ የተሰኘ እጅግ በረሃማ የሆነ ስፍራ ከፊት ለፊታቸው ገጠማቸው ።

Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል፦ DW

የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ ቅሪት ክፍል 1

This browser does not support the audio element.

የጀርመን ቅኝ ገዢ ኃይል ወደ ናሚቢያ እግሩን ያስገባበት አጋጣሚ

በጎርጎርሳውያኑ 1880ዎቹ አውሮጳውያን የካርታ ስራ ባለሞያዎች 2 ሺ ኪሎሜትሮችን በሚያካልለው የባህር ሰርጥ አካባቢ በወቅቱ  ለመርከብ ማቆሚያነት  ሊያገለግሉ የሚችሉ ሶስት አስተማማኝ አካባቢዎችን መለየት ችለው ነበር። ነገር ግን ተጓዞች ከመርከብ ሲወርዱ 140 ኪሎሜትሮች የሚረዝም ናሚብ የተሰኘ እጅግ በረሃማ የሆነ ስፍራ ከፊት ለፊታቸው ገጠማቸው ።

የናማ ጎሳ መሪ የነበረው ጆሴፍ ፍሬድሪክ 2ኛ በ1883 ሄንሪች ፎገልሳንግ የተባለ አንድ ወጣት ጀርመናዊ ነጋዴ ደቡባዊ ናሚቢያ ውስጥ በምትገኘው ቤታኒ ውስጥ ተቀበለ። ወጣቱ ነጋዴ አዶልፍ ሉደሪትስ በተባለ የንግድ ስም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ዳርቻ ለሚገኝ ባህረ ገብ መሬት ለውጥ  ለፍሬድሪክስ 200 ጠመንጃ እና 100 ፓውንድ ስተርሊንግ አቀረበለት። ከጥቂት ወራት በኋላም ሌላ ተጨማሪ ስምምነት ተከተለ። በመልዓምድራዊ ልኬት 20 ማይሎችን ለሚረዝም ፣ ከኦሬንጅ ወንዝ ደቡባዊ አቅጣጫ ለሚገኝ እና እና ከደቡብ አፍሪቃ ለሚዋሰን ተጨማሪ ሰፊ መሬት ለውጥ 60 ጠመንጃዎች እና 500 ፓውንድ ስተርሊንግ ቀረበ ። ይህ የዚያ ሁሉ ምስቅልቅል ታሪክ መነሻ ነው ።#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colonialism 

አዘጋጅ ካይ ኔቤ

ተርጓሚ እና ተራኪ ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW