1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ቅኝ ግዛት እና የድዋላ ስምምነት

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

በ 1871 ጀርመን ስትዋሃድ መራሄ መንግስት ኦቶ ፎን ቢስማክ ቅኝ ግዛቶን እንደ ውድ እና የቅንጦት ነገር በማየታቸው እምብዛም ፍላጎት አላሳዩም ነበር ። ነገር ግን አውሮጳውያኑ ለአፍሪቃ ገበያ ያላቸው ተወዳዳሪነት በማደጉ ምክንያት እንደ ቮርማን አይነት የንግድ ሰዎች መራሄ መንግስቱን የማግባባት ስራ የግድ ብሎ ነበር

Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል DW

በ 1871 ጀርመን ስትዋሃድ  መራሄ መንግስት ኦቶ ፎን ቢስማክ ቅኝ ግዛቶን እንደ ውድ እና  የቅንጦት ነገር በማየታቸው እምብዛም ፍላጎት አላሳዩም ነበር ። ነገር ግን አውሮጳውያኑ ለአፍሪቃ ገበያ ያላቸው ተወዳዳሪነት በማደጉ ምክንያት እንደ ቮርማን አይነት የንግድ ሰዎች መራሄ መንግስቱን የማግባባት ስራ የግድ ብሎ ነበር። በ1883 በምዕራብ አፍሪቃ ሞግዚትነትን ለማቋቋም የሚያስችል ዕቅድም አቀረበ። በእርግጥ ይህን በማድረጉ ሀምሌ 1984 በዱዋላ ንጉሶች ቤል እና አክዋ  የድዋላ ስምምነቶችን እንዲፈርሙ እና  ቮርማንን በካሜሮን መሬት እና ንግዱን በብቸኝነት የመቆጣጠር መብት እንዲጎናጸፍ አስችሎታል። ይህም ለተመሳሳይ አላማ ወደ ድዋላ በመቅዘፍ ላይ የነበረች የታላቋ ብሪታንያ መርከብ ከመድረሷ ሰዓታት አስቀድሞ የጀርመን ሰንደቅ ዓላማ ድዋላ ላይ እንዲውለበለብ አስችሎታል።

መራሄ መንግስት ቢስማርክም ቅኝ ግዛቶችን መያዝ ለጀርመን ህዝብ እና ለሌሎች የአውሮጳ ሀገራት ጀርመን አዲሷ የዓለም ኃያል ሀገር ሆና መምጣቷን ለማሳየት ቀደም ወደ ማያምኑበት የጫወታው ሜዳ ገቡ ።

 የተቃውሞው መቀስቀስ ግን ለቮርማን ምቹ ሁኔታ ፈጠረለት። በዚህም  ለቢስማርክ የቅኝ ግዛቶች አስተዳደር አማካሪ በመሆን   በ 1884/1885 በርሊን ባስተናገደችው እና  የአውሮጳ የቅኝ ግዛት ይገባኛል ጥያቄዎችን ባጸደቀው ጉባኤ ላይ ቁልፍ ተዋናይ መሆን የሚያስችለውን ዕድል ፈጠረለት። ከዚህ መኋላ የቮርማን የንግድ መርከብ ኩባንያ እጅጉን ሲበለጽግ በኋላም የጀርመን መንግስት ኃይል የቀኝ እጅ መሆን ቻለ።

«ሞግዚትነቱ» የጀርመን ኩባንያዎችን እና ገበያዎቻቸውን ከአውሮጳውያኑ ተወዳዳሪዎቻቸው ስለሚጠብቋቸው በጣም ጥሩ ሆኖላቸዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የጀርመን መንግስት አንድ አካል ሲሆኑ ደግሞ በጀርመን ወታደራዊ ኃይል ሊተማመኑ ሁሉ ይችላሉ ። 

 ጀርመን ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶቿ 60 በመቶውን የሚሸፍኑት የአልኮል መጠጦች ናቸው ። የቅኝ ግዛቶቿን ከአካባቢ አማጽያን እና ከሌሎች አውሮጳውያን ኃይላት ለመከላከል ደግሞ የጦር መሳሪያ ይከተላል። ካሜሩናዊው የታሪክ ተመራማሪ ዶ/ር ጊልበርት ንጊምንዶን ስለነዚያ ስማቸው ጎልቶ  ስለሚነሳ የጀርመን ቅኝ ገዢ መኮንኖች እንዲህ ይገልጻሉ።

« ጀርመኖች የካሜሮንን የባህር ዳርቻ አካባቢ ለቀው የመውጣት እቅድ በማውጣት ወደ መካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ዘልቆ በመግባት  የጥሬ ዕቃ አምራቾችን የማግኘት ውጥን ወጠኑ ። ለምሳሌ ጎማ ፣  ብረት ፣ የፓልም ዘይት ፤ መሬትን በማዳበር የሙዝ እና ካካዋ ተክሎችን በስፋት የማልማት ዕቅድ ያዙ፤ ነገር ግን በባህር ጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ጎሳዎች የጀርመኖቹን ውጥን ከመቀበል ይልቅ መከላከልን መርጠዋል። ምክንያቱም  ኤኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትልባቸው ስጋት ገብቷቸዋል  ።

 የጀርመን ኩባንያዎች ከካሜሩኗ የዱዋላ ገዢዎች ጋር የቅኝ ግዛት የንግድን እንቅስቃሴዎችን  በባህር ዳርቻዎች ላይ ብቻ የተገደቡ የማድረግ ውላቸውን ማፍረስ  ጀመሩ ። ይህንኑ ተከትሎም ዱዋላዎች የንግድ መስመር እና መሬት ላይ የነበራቸውን የተቆጣጣሪነት መብት ተነፈጉ ።

በ1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ የቮርማን ኩባንያዎች ከካሜሩን ወደብ ርቀው በመሄድ በማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል የፓልም ዘይት ፣ ካካዋ ፣ የጎማ ፣ የትምባሆ እና የቡና  እርሻዎችን ማቋቋም ችለዋል።

በዚሁ ጊዜ ካሜሩንያን ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል። አዳዲሶቹ እርሻዎች በርካታ የሰው ጉልበት  ይጠይቃሉ፤ እናም በርካታ ወንዶች እና ሴቶች  በእነዚሁ እርሻዎች ላይ ተገደው እንዲሰሩ ተገደርገዋል ፤ ሁኔታዎችም በጭካኔ የተሞሉ ነበር።

 ጭቆናው በብዙ መልኩ የሚገለጽ ቢሆንም  በመሬት ወረራ፣ አዲስ ሕግ በማውጣእና  ከመጠን በላይ ግብር በመጣል የህዝቡን ምሬት ጨምረዋል። የዚህ  ጨቋኝ እና በዝባዥ ኃይል ምልክትም  "50ው " ተብሎ ይታወቃል።

« የምልክቱ ስም በምክንያት ነበር የወጣው ። ለምሳሌ ሰላምታ አለመስጠት ወይም ለነጭ ሰው መንገድ አለመልቀቅ በቆዳ በተሰራ ጅራፍ 50 ጊዜ ያስገርፋል። ይህ በጀርመን ቅኝ ግዛቶች ሁሉ ስራ ላይ የዋለ እና የሚታወቅ ተግባር ሆነ ።»

በወቅቱ የጎማ ንግድ እጅጉን እያደገ የመጣበት ወቅት ነበር ። ለዚህ ነው እንደ ቮርማን ያሉ  የንግድ ሰዎች ወደ ማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ዘልቀው ለመግባት ምክንያት የሆናቸው ። እንደ ዕድል ሆኖ እንደ ጄስኮ ፎን ፑትካመር ያሉ ኃይለኛ የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎች ካሜሩናውያንን 20 ፣ 30 እያደረጉ በመጠርነፍ  የጎማ ምርት እንዲሰበስቡና ከመሃል ሀገር ወደ ወደቦች በሸክም እንዲያጓጉዙ ያስገድዷቸው ነበር። ካሜሩናውያኑ ይህንኑ የግዳጅ ስራ እንዳያምጹ የጀርመን ወታደሮች እርምጃ ለመውሰድ በቅርብ ርቀት ይጠባበቁ ነበር።

ይህም ለመንደሮች መቃጠል እና ሰዎች ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ተነጥለው የከፋ ስቃይ ወደ ሚጠብቃቸው የባህር ዳርቻ አካባቢዎች እንዲወሰዱ ምክንያት ሆነ። አንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸውን ዳግም ላያገኙ እስከወዲያኛው ሲያሸልቡ አንዳንዶቹ ደግሞ በአስጨናቂ ሕይወት ውስጥ ለመኖር ተገደዱ። ጀርመኖቹ የሀገሬውን ባህል እና ወግ ገፍተው ፣ መንደሮችን አቃጥለዋል፣ የጎሳ መሪዎችን በአደባባይ ገርፈው አዋርደዋል፣ ማህበረሰቡን አፈናቅለው ለስደት ዳርገዋል።

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW