የጀርመን እርዳታ ለኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2009ማስታወቂያ
የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ ። እርዳታው በኢትዮጵያ ለሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መርጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሚቀርብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚውል ተገልጿል።ለነዚሁ ሰብዓዊ እርዳታዎች ጀርመን በአጠቃላይ 3.6 ሚሊዮን ዩሮ መመደቧን በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ አስታውቋል።የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስለ ተጨማሪው ሰብዓዊ እርዳታ የኤምባሲውን የፕሬስ ጉዳዮች ሀላፊን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ