1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

የጀርመን ኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልውውጥ እመርታ

ቅዳሜ፣ መስከረም 28 2015

ኢትዮጵያ እና ጀርመን በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ከግዜ ወደ ግዜ እየጠነከረ መምጣቱ ተገለጸ ። የጀርመን የከፍተኛ ትምህርት ልውውጥ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት ኢትዮጵያ እና ጀርመን በተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በ መምህራን ጭምር ግ ንኙነታቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

Addis Ababa | Ethiopian-German academic relations meeting
ምስል Hanna Demissie/DW

የጀርመን ኢትዮጵያ የትምህርት ልውውጥ ተሞክሮ ተካሂዷል

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ እና ጀርመን  በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ከግዜ ወደ ግዜ እየጠነከረ መምጣቱ ተገለጸ ። የጀርመን የከፍተኛ ትምህርት ልውውጥ አገልግሎት  በኢትዮጵያ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች  ጋር ባደረገው ውይይት በኢትዮጵያ  የጀርመን አንባሳደር  ስቲቨን  አውር ኢትዮጵያ እና ጀርመን በተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በ መምህራን ጭምር ግ ንኙነታቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል።  ለዚህም የትምህርት ሚንስትርን ሲያመሰግኑ  በሴሚናሩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚንስትር የትምህርት ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ኤባ ሚጂና ትምህርት ሚንስቴር አዲስ እየሰራው ላለው ስረዓተ ትምህርት የጀርመንን ተሞክሮ ማየታቸው ጠቃሚ ልምድ እንደሆናቸው ተናግረዋል ።

ምስል Hanna Demissie/DW

ላለፉት 11 አመታት በኢትዮጵያ ከከፍተኛ ትምህርት እድል ጋር ሲሰራ የቆየው የጀርመን የከፍተኛ ትምህርት  ልውውጥ አገልግሎት  በኢትዮጵያውያን እና በጀርመን የትምህርት ግንኙነት ባደረገው ውይይት በሀገራችን  የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው  ባለሙያዎች ለተጨማሪ የዶክትሬት ትምህርት እና የምርምር ስራ መስራት  በጀርመን ያሉ የምርምር ተቋማትን እና ሌሎችም  የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቁዋማትን አስተዋውቋል ።

በሴሚናሩ ላይ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የነፃ ትምህርት እድል  በጀርመን አግኝተው የነበሩ  ዶክተሮች  እና ፕሮፌሰሮች  ልምዳቸውን እና ተሞክሯቸውን  በውይይቱ ላይ ለተገኙት የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች አቅርበዋል ፕሮፌሰር አለምጸሐይ መኮንን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተወክለው በልምድ ልውውጡ ላይ የተገኙ እንዳሉት  ይህ የጀርመን ትምህርት ልውውጥ አገልግሎት  በሀገራችን ለበለጠ ትምህርት እና የምርምር ስራ የሚሰጠው  እድል ከፍተኛ እንደሆነ  ነው ለ DW የገለጹት። በሴሚናሩ ላይ የጀርመን ትምህርት  ልውውጥ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን አውሮፓ ህብረት ጭምር  ለኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች እና የዶክትሬት ዲግሪ መማር ለሚፈልጉ ያለውን እድል እና እገዛ ለተቋማቱ ኃላፊዎች አስረድተዋል።

ሃና ደምሴ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW