1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እና የምዕራብ አፍሪቃ ቀጣዩ የትብብር መንገድ

ዓርብ፣ የካቲት 3 2015

የምዕራብ አፍሪካ መረጋጋት ለአውሮፓ ደህንነት አስፈላጊ መሆኑን የጀርመን የገንዘብ ሚኒስትር ክርስቲያን ሊንደርነር ገለፁ። ሚንስትሩ በተለይ ለDW እንደገለፁት አፍሪካን ለማረጋጋት ጀርመን ከወታደራዊ ድጋፍ ይልቅ በኢኮኖሚ ድጋፍ ላይ ታተኩራለች።

Ghana Accra Finanzminister Christian Lindner
ምስል Isaac Kaledzi/DW

ጀርመን በአፍሪቃ ከወታደራዊ ይልቅ በኢኮኖሚ ትብብር ላይ ልታተኩር ነው

This browser does not support the audio element.


የጀርመን የገንዘብ ሚኒስትር ክርስቲያን ሊንደርነር የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ አካል ሆኖ ማሊ የሰፈረውን የጀርመን ጦር በቅርቡ በጎበኙበት ወቅት የምዕራብ አፍሪካ መረጋጋት ለአውሮፓ ደህንነት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። 
ሊንደርነር  በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በጋኦ ዳርቻ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወታደራዊ ጣቢያ ሲጎበኙ፡ ለስኬት ወሳኙ ነገር የእኛ ተሳትፎ በባማኮ በመንግስት መደገፉ ነው።ሲሉም ተደምጠዋል።
እሳቸው ይህን ባሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ ግን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ  ማሊን ጎብኝተዋል። 
ከአውሮፓ ጋር ያለው ግንኙነት ከመሻከሩ ጋር ተያይዞ  ከሩሲያ ጋር ያላትን ወዳጅነት እያጠናከረች የመጣችው ማሊን ጨምሮ በምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት  ጀርመን  ከወታደራዊ ድጋፍ ይልቅ በኢኮኖሚ ድጋፍ ላይ እንደምታተኩር ከርስትያን ሊንድነር በዚህ ሳምንት ከDW ጋረ ባደረጉት ቃለምልልስ ገልፀዋል 
«ጀርመን ለሁሉም የአፍሪካ ማህበረሰቦች አስተማማኝ አጋር ነች። በምዕራብ አፍሪካ መረጋጋት እንዲሰፍን ፍላጎት አለን። ምዕራብ አፍሪካ የተረጋጋ ከሆነ የአውሮፓ ህብረት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ስለዚህ ከምዕራብ አፍሪካ ማህበረሰብ ጋር ያለንን ግንኙነት ማሳደግ እንፈልጋለን። ይህ ማለት ግን በወታደራዊ ድጋፍ ላይ እናተኩራለን ማለት አይደለም። ነገር ግን ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ እናጠናክራለን ። ኢኮኖሚያዊ መሠረት ካለ፣  በደህንነት ጉዳዮች ላይ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል።»በማለት ገልጥፀዋል።
ክርስቲያን ሊንድነር  በዚያው ቃለ ምልልስ ለDW እንደተናገሩት የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ማድረግ አሁን ያለው የበርሊን ጥምር መንግስት ቀዳሚ ተግባር  መሆኑንም ገልፀዋል። እንደ ሚንስትሩ  ታዓማኒነት አና ቀጣይነት ያለው ገበያ ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አያይዘውም አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ቀውስ  ለመፍታት  ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ላይ በማተኮር  ሕዝቡ ተጨማሪ ዕድገት እንዲፈጠርለት  ማድረግን ጨምሮ መንግስታቸው የተለያዩ ርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልፀዋል። 
ለዚህ መሰሉ  የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትም ጋናን በመሳሰሉ  የምዕራብ የአፍሪቃ ሀገራት የተመቸ  ሁኔታ መኖሩን ሚንስሩ ገልፀዋል። ይህ የኢኮኖሚ ትብብርም «ኮምፓክትዊዝ አፍሪካ» በተባለው ማዕቀፍ ስር እንደሚሆንም  አብራርተዋል።
«በግሌ ጋና ውስጥ ብዙ ሥራ ፈጣሪዎችን በጀርመን ኩባንያዎች ውስጥ አግኝቻለሁ። እዚህ ባለው ገበያ ላይ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ናቸው።  ስለዚህ  «ኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ»  ገበያችንን ሀበረተሰባችንን  ሀገራችንን እርስ በእርስ ለማቀራረብ  የመጀመሪያው  አስፈላጊ ርምጃ ነው። ስለዚህ  በጋና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና እድገት ላይ ትልቅ ፍላጎት አለን።» በማለት የኢኮኖሚ ትብብሩን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
ማሊ ፊቷን ወደ ሩሲያ ባዞረችበት በዚህ ወቅት  ጀርመን ጦሯን ከሀገሪቱ ታስወጣ እንደሁ ለቀረበላችው ጥያቄም ከማሊ ምርጫ በኋላ በተያዘው ቀነ ገደብ ጦሩ ለቆ እንደሚወጣ ሚንስትሩ ገልፀዋል።
ከጎርጎሪያኑ ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ከ1,100 በላይ ወታደሮችን  በተባበሩት መንግስታት  ተልዕኮ ስር  በማሊ አሰማርታ የቆየችው ጀርመን  በጎረጎርያኑ ግንቦት 2024 ዓ/ም ጦሯን ከሀገሪቱ  ታስወጣለች ተብሎ ይጠበቃል።

ምስል Michele Cattani/AFP/Getty Images


ፀሐይ ጫኔ
እሼቴ በቀለ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW