የጀርመን እጩ ተፎካካሪዎች ክርክር
ሰኞ፣ ነሐሴ 29 2009ማስታወቂያ
አራት አወያዮች በተሰየሙበት ክርስቲያን ዴሞክራቷ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና ሶሻል ዴሞክራቱ ተፎካካሪያቸዉ ማርቲን ሹልስ ያካሄዱት ክርክር ዋናዉ ትኩረቱ የስደተኞች በጀርመን ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋህደዉ የመኖራቸዉ ጉዳይ ላይ እንደሚሆን ቢጠበቅም ፖለቲከኞቹ ጉዳዩን እንዳድበሰበሱት ነዉ ተንታኞች የሚናገሩት። ክርክር በኋላ የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት ምዘና አንጌላ ሜርክል የተሻለ ተወያይ እንደነበሩ መጠቆሙም ተገልጿል። እንዲያም ሆኖ ሸዋዬ ለገሠ ያነጋገረቻቸዉ እዚህ ጀርመን ሀገር የሚኖሩት የሕግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ክርክሩ ኅብረተሰቡ ከሚፈልገዉ ሀገራዉ ጉዳይ ይልቅ በዉጭ ጉዳይ በመሸፈኑ ብዙም የሕዝቡን ትኩረት መሳብ ተስኖታል ይላሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ