የጀርመን ከዓለም እግር ኳስ ግጥሚያ መሰናበት
ዓርብ፣ ሰኔ 22 2010ማስታወቂያ
ደቡብ ኮርያ ጀርመንን ሁለት ለባዶ ነው የረታችው። የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በዙር ግጥሚያ ሲሰናበት ከብዙ ዓመታት ወዲህ የትናንቱ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። የአራት ጊዜ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን ለዚህ ዓይነት ሽንፈት መድረሷ ብዙዎችን አስገርሟል። በቀድሞ የዶይቸ ቬለ የአማርኛ ክፍል ስፖርት አዘጋጅ መስፍን መኮንን አስተያየት፣ የ2014 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ሻምፒዮን የነበረችው ጀርመን ይህ ዓይነት በጊዜ የመሰናበት ሁኔታ ሊያጋጥማት የቻለው ተጫዋቾቹ ከልብ የትግል ፍላጎት አለማሳየታቸው እና የማጣሪያ ጨዋታዎችን ሁሉ በማሸነፋቸው ምናልባትም የማይበገሩ የመሆን ስሜት አድሮባቸው ሊሆን ይችላል።
መስፍን መኮንን/አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ