የጀርመን የአቶም ሐይል ማዕከላት የስራ ጊዜ መራዘም ያስነሳው ውዝግብ
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2002ማስታወቂያ
ሀገሪቱን የሚመራው የእህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራቶች ህብረትና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች እንዲሁም የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ተጣማሪ መንግስት የጀርመን የአቶም ኃይል ማመንጫዎችን ዕድሜ በአማካይ በአስራ ሁለት ዓመት ለማራዘም ወስኗል ። ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጀርመን የኒዩክልየር ኃይል ማመንጫዎችን ለመዝጋት ከዚህ ቀደም የተያዘው ዕቅድ ወደ ኃላ መቀልበስ የለበትም ሲሊ ተቃውሞአቸውን በማሰማት ላይ ናቸው ። መንግስት በበኩሉ አሁን ስራ ላይ ያሉትን የኒዩክልየር ጣቢያዎች ለመዝጋት ጊዜው ገና ሲል ይከራከራል ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ