ሰለሞን ሙጬ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2018ጀርመን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በምስራቅ አፍሪቃ በተለይም በአፍሪቃ ቀንድ ምንድን ነው? የሚለውን በአጭሩ ለመግለጽ ያኽል ፦ የመጀመርያው አካባቢው ወይም ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ያለው እንዲሆን ይፈለጋል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ጋር ተያይዞ ውጥረቶች እንዳሉ ይታወቃል። ጀርመን በዚህ ረገድ ጉዳዩ በሰላማዊ መልኩ የሚፈታ ከሆነ እንደሚደግፍ ለማወቅ መቻሉን የአዲስ አበባ ዘጋቢያች ከቤርሊን ከተማ ገልጧል ።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ፤ ዶይቸ ቬለ (DW) ቤርሊን