1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አተገባበር እና ልዩ መገለጫው

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2018

ቡንደስታግ የሀገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት ሕግ አውጪ አካል ነው። ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ቻንስለር ይመርጣል፣ የፌደራል መንግሥትንም ይቆጣጠራል። ቡንደስራት የሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ከሚመሩ 16 ከፍተኛ ዳኞች መካከል ስምንቱን ይመርጣል። አባላቱም ከ16 የፌዴራል ክልሎች የተውጣጡ ናቸው።

የጀርመን የፌዴራል ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፤ ቤርሊን ከተማ
የጀርመን የፌዴራል ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፤ ቤርሊን ከተማ ከፊት ለፊትምስል፦ Solomon Muche/DW

የቡንደስታግ እና ቡንደስራት (የኹለቱ ምክር ቤቶች) ልዩነት

This browser does not support the audio element.

ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ሥርዓት የምትከተለው ጀርመን  ቡንደስታግ የሚባለው የታችኛው ምክር ቤት ወይም ብሔራዊ ሕግ አውጪ አካል ሲሰበሰብ ከላይ በመስታወት የተሠራው ጉልላት ለጎብኝዎች የተዘጋ አይደለም። ይህ የሚደረገው ሕዝብን ወክለው በአዳራሹ የሚገቡ ሰዎች እና ምክር ቤቱ በራሱ ምንጊዜም "በሕዝብ ዐይን ሥር መሆን አለበት" የሚለውን ሐሳብ ለማስተላለፍ ነው። 
በሌላ በኩል የጀርመን 16 የፌዴራሉ አካል የሆኑ ግዛቶችን የሚወክለው ቡንደስራት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚመሩ 16 ከፍተኛ ዳኞች መካከል ስምንቱን ይመርጣል። ለመሆኑ የጀርመን የፌዴራሊዝም አወቃቀር እና አተገባበር ምን የተለዩ ባሕርያት አሉት? 

የቡንደስታግ እና ቡንደስራት (የኹለቱ ምክር ቤቶች) ልዩነት

ጀርመን ጠንካራ የፌዴራል የሥነ መንግሥት አወቃቀር ካላቸው ጥቂት ሀገራት አንዷ እንደሆነች ይታመናል።  ቡንደስታግ የሀገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት ወይም ብሔራዊ ሕግ አውጪ አካል ነው። ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ቻንስለር ይመርጣል፣ ቻንስለሩ የሚመሩትን መንግሥትም ይቆጣጠራል። ቡንደስታግ የተቋቋመው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውድመት በኋላ በ1949 የጀርመን የፌዴራል ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት ሆኖ ነው። ጀርመን ፍትሐዊ ውክልናን ለማረጋገጥ ሁለት ድምጽ - አንድ እጩ እና አንድ ፓርቲ - ለዜጎች በመስጠት የተቀላቀለ አባል ተመጣጣኝ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓትን ትጠቀማለች።

አብዛኛው የሕግ ማውጣት ሂደት የሚከናወነው በልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ነው።

የቡንደስታግ ጉባኤ ለሕዝብ ክፍት ሲሆን ዜጎች ክርክሮችን እንዲመለከቱ፣ አቤቱታዎችን እንዲያቀርቡ እና ከሕንፃው ላይ ያለውን የመስታወት ጉልላትን እንዲጎበኙ ያስችላቸዋል። "ጎብኚዎች ከላይ ሆነው ዲሞክራሲን ቃል በቃል ማየት የሚችሉባቸው በዓለም ላይ ካሉት ጥቂት ፓርላማዎች አንዱ ነው።" ተብሎም ይገለፃል። የቡንደስታግ የፓርላማ ሕንፃ ጀርመን ለዴሞክራሲ፣ ለግልጽነት እና ለዜጎች ተሳትፎ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ምልክት እንደሆነም ይነገራል። በሌላ በኩል የጀርመን 16 የፌዴራሉ አካል የሆኑ ግዛቶችን የሚወክለው ቡንደስራት የሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ከሚመሩ 16 ከፍተኛ ዳኞች መካከል ስምንቱን ይመርጣል። 

የጀርመን የፌዴራል ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የላይኛው ምክር ቤት የሆነው ይህ ተቋም በቀጥታ ሕዝቡን ሳይሆን 16ቱን የፌዴራል ክልሎች ይወክላል። አባላቱ በቀጥታ የተመረጡ ሳይሆን፣ ከክልል መንግሥታት የተውጣጡ ተወካዮች ናቸው።

እያንዳንዱ ክልል ያለው የድምጽ ብዛት የሚወሰነው በሕዝብ ብዛት ነው።

ምክር ቤቱ የፌዴራል ሕጎችን በማውጣት ላይ ይሳተፋል። አንዳንድ ሕጎች ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ ሊተላለፉ አይችሉም። በብሔራዊ ፖሊሲ ውስጥ የክልል ጥቅሞችን ለመጠበቅም ይረዳል። በቀላል አነጋገር ቡንደስራት የጀርመን ክልሎች በፌዴራል ሕግ አውጪነት የሚሳተፉበት ተቋም ነው።

የቡንደስታግ ጉባኤ ለሕዝብ ክፍት ሲሆን ዜጎች ክርክሮችን እንዲመለከቱ፣ አቤቱታዎችን እንዲያቀርቡ እና ከሕንፃው ላይ ያለውን የመስታወት ጉልላትን እንዲጎበኙ ያስችላቸዋልምስል፦ Solomon Muche/DW

ሁለቱ ምክር ቤቶች በዓመት ምን ያህል ጊዜ ይሰበሰባሉ?

በጀርመን ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ውስጥ ዐቢይ የሆኑት ሁለቱ ምክር ቤቶች ማለትምየፌዴራሉ ምክር ቤት ቡንደስታግ  በዓመት 17 ጊዜ ይሰበሰባል፣ የሀገሪቱ ዓመታዊ በጀት ላይ ለመወያየት እና ለማጽደቅ ደግሞ የአንድ ሳምንት ልዩ ስብሰባ ያደርጋል። ክልሎቹን የሚወክለው ቡንደስራት ደግሞ በዓመት ለ11 ጊዜ ይሰባሰባል። የፌዴራሉ አባል ክልሎች በጣም ጠንካራ እና ራስ ገዝነታቸው በተለይ የራሳቸውን ፖሊስ፣ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ፖሊሲ እና ሕገ መንግሥት በማቋቀም ይተገብራል። 

ንስር የጀርመን ፌዴራላዊ ሥርዓት ብሔራዊ ምልክት ነው። 

ንስር የጀርመን ፌዴራላዊ ሥርዓት ብሔራዊ ምልክት ነው። የሀገሪቱ የኃይል፣ የሉዓላዊነት እና የአንድነት ምልክት ሲሆን በሁሉም የፌዴራል ተቋማት ላይ ይንፀባረቃል። የጀርመን ፓስፖርት፣ የመንግሥት ሕንፃዎች፣ የገንዘብ ኖቶች እና ሳንቲሞች እና ይፋዊ የመንግሥት ሰነዶች እንዲሁም የፓርላማ ሕንፃ ላይ ጭምር ይገኛል።

በፓርላማው ሕንፃ ውስጥ የአዶልፍ ሂትለርን ጨምሮ ከ1919 ጀምሮ የነበሩ ታሪካዊ ትርጉም ያላቸው ዋና ዋና የፓርላማ አባላት ስም ለጉብኝዎች ተቀምጧል። ይህም ጎብኝዎች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ግንዛቤ እንዲይዙ ታስቦ የተደረገ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። የፓርላማውን ሕንፃ በቀን 8 ሺህ ሰዎች ይጎበኙታል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW