1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዳግም ውህደት 21 ኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ መስከረም 23 2004

የጀርመንን መዲና በርሊንን ለ 29 ዓመታት ለሁለት ከፍሎ የቆየውን ግንብ መፍረስ የተከተለው የሁለቱ ጀርመኖች ውህደት ለብዙዎች ያልታሰበ ግን በጀርመናውያን ልብ ውስጥ ተደብቆ የቆየ ምኞት ነበር ።

ግንቡ ሲፈርስምስል AP

ጀርመን እ.ጎ.አ በ 1945 በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሸንፋ በተጓዳኝ ኃይሎች እጅ ከወደቀች በኃላ ሳይውድ በግድ ለሁለት የመከፈል እጣ የገጠመው የጀርመን ህዝብ ውህደቱን ላፋጠነው ለበርሊን ግንብ መፍረስ ትላቅ ግምት ነው የሚሰጠው። የበርሊን ግንብ ሲፈረስ የህዝቡ ደስታ ወሰን አልነበረውም ። በዚህ ታሪካዊ ወቅት የጀርመናውያን ደስታ ከተጋሩት አንዱ ኢንጅነር እሸቱ ወንዳፍራሽ ናቸው ። እ.ጎ.አ በ 1980 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው ጀርመን የመጡት ። የበርሊን ግንብ ሲፈርስም ጀርመንና ቤልጂግ ድንበር ላይ በምትገኘዋ በምዕራብ ጀርመንዋ በአኽን ከተማ ነበሩ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW