1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ፕሬዚደንት የአፍሪቃ ኅብረት ጉብኝት

ረቡዕ፣ ጥር 22 2011

በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ረፋዱን በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጽህፈት ቤትን ጎብኝተዋል።

Besuch von Bundespräsident Steinmeier in Äthiopien
ምስል Deutsche Botschaft in Addis Abeba

በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ረፋዱን በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጽህፈት ቤትን ጎብኝተዋል። ፕሬዝዳንቱ በጽህፈት ቤቱ እየተካሄደ ባለው የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መከላከል አውደ ጥናት ላይም ተሳትፈዋል። ዓውደ ጥናቱ ግጭትን በመከላከል ረገድ በአፍሪካ እና በአውሮጳ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የተገኙ ትምህርቶች የሚዳሰሱበት ነው። 

ምስል Deutsche Botschaft in Addis Abeba

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ባለፈዉ እሁድ ምሽት አዲስ አበባ የደረሱት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ረቡዕ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ላሊበላ ከማቅናታቸው በፊት በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚደረግለትን የፌደራል ቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩትም ጎብኝተዋል። በላሊበላ ቆይታቸውም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ኾነው መልእክት አስተላልፈዋል። 

ምስል Deutsche Botschaft in Addis

«ትናንት አዲስ አበባ ከፕሬዚዳንቷ፣ ከጠቅላይ ሚንሥትሩ፣ እንዲሁም በሀገሪቱ በሚታየው የፖለቲካ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከኾኑ በርካታ ሰዎች ጋር በፖለቲካ ንግግር የተሞላ ቀን ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ ታላቅ በዓል ነው። የማርያም እረፍት ቀን። እናም አጋጣሚውን በመጠቀም እዚህ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተናል። ከጠቅላላው የጀርመን ልዑካን ጋርም በዓለም ቅርስ የተመዘገበችውን ከተማ እየተመለከትን ነው።» ጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ምሽት ላይ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ወደ ሃገራቸዉ ይመለሳሉ።     

ተስፋለም ወልደየስ 

አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW