1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ መጀመር

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2016

በኦሮሚያ ክልል በሞጆ ከተማና አዳማ ከተማ መካከል በተለያዩ ምእራፎች የሚገነባ የተባለው የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በይፋ የስራ ማስጀመር መርሃግብር ተከናወነ፡፡ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው ሞጆ ከተማ አቅራቢያ የተለያዩ ኢንደስትሪዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ግዙፍ መንገዶች፣ የሎጂስቲክ ማእከላትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይገነቡበታል፡፡

ዐቢይ አህመድ: የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ዐቢይ አህመድ: የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምስል Seyoum Getu/DW

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ መጀመር

This browser does not support the audio element.

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ መጀመር

በኦሮሚያ ክልል በሞጆ ከተማ እና አዳማ ከተማ መካከል በተለያዩ ምእራፎች የሚገነባ የተባለው የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዛሬው እለት በይፋ የስራ ማስጀመር መርሃግብር ተከናወነ፡፡

ከመዲናዋ አዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ግድም ርቃ በምትገኘው ሞጆ ከተማ አቅራቢያ የተለያዩ ኢንደስትሪዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ግዙፍ መንገዶች፣ የሎጂስቲክ ማእከላት እና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይገነቡበታል የተባለው ይህ ማዕከል 24 ሺህ ሄክታር ስፋት ያለው መሬት ላይ እንደሚያርፍም ተጠቁሟል፡፡

የነዳጅ እጥረት በኦሮሚያ ክልል

በዛሬው ፕሮጀክቱን የማስጀመር መርሃግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መሰል የነጻ ኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ጅማሮ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በትኩረት ስትገነባቸው ከነበረው የኢንደስትሪ ፓርኮች ወደ ሌላ አማራጭ ፊቷን ማዞሯን እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡

ከአራት ዓመታት በፊት መመስረቱ የተነገረው ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ኢንደስትሪዎች፣ የመዝናኛ ማዕከከላት፣ ወደ ውጪ ገቢያ የሚላኩ ምርቶች ማምረቻ ማዕከላት እና ነጻ የንግድ ቃጣና የሚኖሩት ዘመናዊ ከተማ ነው ተብሏል፡፡ ዛሬ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (CCECC) ከተሰኘው የቻይና ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ውል በማሰር ወደ ስራ የገባው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ፤ ማእከሉ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ አገራዊ ገቢ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን እንደሚያበረታታ መታመኑን አመልክቷል፡፡

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ መጀመርምስል Seyoum Getu/DW

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ክላስተሮች

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስከያጅ ሞቱማ ተመስገን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የኢኮኖሚ ዞኑ በዓለም የሚታወቅ የኢኮኖሚ ማዕከል ይሆናል፡፡ “የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓለም የሚታወቅ የኢኮኖሚ ማዕከል የመገንባት ረጅም ራዕይ አለው፡፡ የዞኑ ዓላማ ዓለም በገባበት በዚህ 5ኛው የኢንደስትሪ አብዮት ወቅት ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ የውጪ ምንዛሪ ማስገኘት የአገር ገቢ ማሳደግ፣ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ የከተሞች እድገት ላይ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢኮኖሚ ዕድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡

ይህ የኢኮኖሚ ዞን በ24 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እንደ የሎጂስቲክ ማዕከል፣ ነጻ የንግድ ቀጠና፣ የሪልስቴት ልማት፣ የቱሪዝም እና መዝናኛ ማዕከላትን የመሳሰሉ በርካታ የኢኮኖሚ ክላስተሮችን ያቀፈ ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ዞኑን ልዩ የሚያደርገው” ብለዋል፡፡

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት የሰላም ጥሪ፣ ተስፋና ስጋቱ

የኢኮኖሚ ዞኑን በአራት ምዕራፍ ለማልማት መታቀዱም ተነግሯል፡፡ በዛሬው እለት ከኢኮኖሚ ዞኑ ጋር የመግባቢ ስምምነት ያኖረው የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የወጪ ምርት ማምረቻ እና ሎጂስቲክን በጋራ ለማልማት 100 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱም ነው የተገለጸው፡፡ አልሚው ኩባንያ CCECC ም በስምምነቱ ወቅት በአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን የኢኮኖሚ ማዕከል ለመገንባት ቃል ገብቷል፡፡

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ መጀመርምስል Seyoum Getu/DW

ከኢንደስትሪ ፓርኮች ወደ ነጻ የንግድ ቃጠናዎች፡ የፖሊሲ ለውጥ

በዛሬው ማዕከሉን ስራ የማስጀመር መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መሰል ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ በስፋት ስገነባ ከነበረው የኢንደስትሪ ፓርኮች ላይ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ “የኢንደስትሪ ፓርኮችን በብድር እየገነባን ለውጪ ዜጎች ብቻ የተከለለ እያደረግን የኢትዮጵያን ኢንደስትሪ መለወጥ አንችልም፡፡ በፖሊሲ ለውጥ ያመጣንብት አንዱ ነገር የኢንደስትሪ ፓርኮችን በብድር ከመገንባት ነጻ የንግድ ቀጠናን ለግሉ ማህበረሰብ አስቻ ሁኔታ በመፍጠር የውጪና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ተጋግዘው ሳፋፊ ኢንደስትሪ የሚገነቡበት አውድ መፍጠር ነው” ብለዋል፡፡ ይህ የፖሊሲ ለውጥ ከተደረገ በኋላ በድሬዳዋ ከተመሰረተው ነጻ የንግድ ቀጠና ቀጥሎ ይህ በሞጆ እና አዳማ መካከል የሚገነባው የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በቀጣይነት የተጀመረው የንግድ ቀጠና ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ስራ የጀመረው የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሰፋፊ እድሎች ያሉት ሲሉ ማእከሉ የተገነባበት ስፍራ አመቺነት አስረድተዋልም፡፡ “ፈጣን መንገድ፣ በቂ ኃይል፣ የሰለጠነ የሰው አቅም፣ በቂ የግብርና አቅርቦት” የኢኮኖሚዞን የኢንደስትሪ ክላስተርን በኤነተኛ መልኩ ሊያግዙት እንደሚችሉም አብራርተዋል፡፡

 

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW