የገዳ ቢሊሱማ ፓርቲና የምርጫ ቦርድ ውዝግብ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2013
ማስታወቂያ
የገዳ ስርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ-ገዳ ቢሊሱማ በ2012 በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመሰረዝ ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ የተገለልኩት ያለአግባብ በመሆኑ ቦርዱ በምርጫው እንዲሳተፍ ዳግም ሁኔታዎችን ሊያመቻችልኝ ይገባል ሲል አመለከተ፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት በቦርዱ እውቅና ተነፍጎ የተሰረዘው ፓርቲው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ሚያዚያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ በሚል ስያሜው አገር አቀፍ ፓርቲ መሆኑ ቀርቶ የገዳ ስርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ/ገዳ ቢሊሱማ በሚል መጠሪያ በክልል ፓርቲነት ሊመዘገብ ይገባል ብሏል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሮበሌ ታደሰ ለዶይቼ ቬሌ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በማመልከት ለስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ ለመሳተፍ መጠየቁንና ምርጫውም እንዲራዘም ሃሳብ ቢያቀርብም ያገኘው ምላሽ የለም፡፡ በመሆኑም የፍርድ ቤት ውሳኔ ገቢራዊ እንዲሆንልን እንሻለን ይላል ፓርቲው፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ አሁንም ይግባኝ ጠይቀበታለሁ ብሏል፡፡
ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ