1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉራጌ ተወላጆች ሠልፍ በሀዋሳ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 10 2015

በጉራጌ ዞን 4 ወረዳዎችና 3 የከተማ አስተዳደር ነዋሪ ተወካዮች «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን » የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። አባላቱ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮችን ባካተተ የዞን መስተዳድር ለመደራጀት ጠይቀዋል።

የጉራጌ ተወላጆች ሠልፍ በሀዋሳ
በጉራጌ ዞን አራት ወረዳዎችና ሦስት የከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን» የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሰላማዊ ሠልፍ ጠየቁ።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ቅሬታ ያስነሳው የክላስተር ከተሞች አደረጃጀት

This browser does not support the audio element.

 

በጉራጌ ዞን አራት ወረዳዎችና ሦስት የከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን» የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሰላማዊ ሠልፍ ጠየቁ። አባላቱ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮችን ባከተተ በአዲስ የዞን መስተዳድር ለመደራጀት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። የሠልፈኞቹን ተወካዩች ተቀብለው ያነጋገሩት የክልሉ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ጥያቄው አዲስ በሚደራጀው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል ብለዋል።  

የጉራጌ ተወላጆች ሠልፍ በሀዋሳ

በጉራጌ ዞንአራት ወረዳዎችና ሦስት የከተማ አስተዳደር ነዋሪ ተወካዮች  «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን » የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። አባላቱ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮችን ባካተተ የዞን መስተዳድር ለመደራጀት ጠይቀዋል። ሠልፈኞቹ የያዟቸው መፈክሮቹ የጉራጌ ዞን ሥር ከሚገኙ የአስተዳደር መዋቅሮች መካከል አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮች «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን» የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀር የሚጠይቁ ናቸው።

«ምሥራቅ ጉራጌ ዞን»

«የምሥራቅ ጉራጌ ዞን» በሚል በአዲስ ዞን እንዲዋቀሩ ሠልፈኞቹ ጥያቄ ያቀረቡባቸው የመስቃን፣ የምሥራቅ መስቃን፣ የሶዶ፣ የቡኢ ወረዳዎችና እንዲሁም የቡታጅራ፣ የሶዶ እና የኢኒሴኖ ከተማ አስተዳደሮች  ናቸው፡፡ በሀዋሳው ሠልፍ ላይ የታዳሙት ከአራቱ ወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች የተወከሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መሆናቸውን የሠልፈኖቹ ተወካዮች ገልጸዋል።

ሠልፈኞቹ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ አራት የወረዳ እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮችን ባካተተ የዞን መስተዳድር ለመደራጀት ጠይቀዋል።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ከሠልፈኞቹ ተወካዮች መካከል ወይዘሮ ውዴ ጫካ እና አቶ ወንደወሰን ኃይሌ «ኅብረሰቡ የራሱን ዞን ለመመሥረት የፈለገው ባለፉት 30 ዓመታት የልማት ተጠቃሚ ባለመሆኑ ነው» ብለዋል። «በአራቱ ወረዳዎች እና በሦስቱ የከተማ አስተዳደሮች የምንገኝ ነዋሪዎች የፍትህና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት አደጋች ሆኖብን ቆይቷል» በማለት የጠቀሱት የሠልፈኞቹ ተወካዮች «የፍትህና ሌሎች አገልግሎቶችን ፍለጋ የዞኑ የአስተዳደር መቀመጫ ወደ ሆነችው ወልቂጤ ከተማ ድረስ ረጅም ኪሎሜትሮችን በመጓዝ ለእንግልትና ለወጪ ስንዳረግ ቆይተናል። አሁን ግን አገልግሎቱን በአቅራቢያችን የምናገኝበት ሁኔታ ሊመቻች ይገባል። ይህ የሚሆነው ደግሞ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮችን ያቀፈ የዞን መስተዳድር ሲዋቀር በመሆኑ ይኼው ተግባራዊ እንዲሆንልን በሰላማዊ መንገድ እየጠየቅን እንገኛለን» ብለዋል።

የክፍፍል ሥጋት  

«የምሥራቅ ጉራጌ ዞን» በሚል በአዲስ ዞን እንዲዋቀርላቸው የጠየቁት የሠልፈኞቹ ተወካዮች ወይዘሮ ውዴ ጫካ እና አቶ ወንደወሰን ኃይሌ የዞን አደረጃጀት ጥያቄው የተነሳው ዛሬ ሳይሆን በ1985 ዓም ነበር ይላሉ። ይሁንአንጂ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እየተንከባለለ አሁን ያለበት ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል። ጥያቄያችሁ በጉራጌ ማኅበረሰብ መካከል ክፍፍል አይፈጥርም ወይ?  የአስተዳደራዊ መዋቅር ጥያቄዎች ጥቂት የሥልጣን ሹመኞችን ምቾት ከማስጠበቅ ባለፈ ለህዝቡ ምን ያስገኝለታል ትላላችሁ?  በሚል ዶቼ ቬለ DW የሠልፈኞቹን ተወካዮች ጠይቋል። ከሠልፈኞቹ ተወካዮች አንዱ አቶ ወንደወሰን « ይህ አንዳንድ አሉባልተኞች የሚያስወሩት ወሬ ነው» ይላሉ። «ጥያቄው የልማትና የመልካም አስተዳደር እንጂ ህዝብን የሚበትን አይደለም። በአጠቃላይ አስተሳሰቡ ፍጹም ስህተት ነው» ብለዋል። ሁልጊዜ የመዋቅር ጥያቄውን ስናነሳ የጥቂት አመራሮች ፍላጎት ነው እየተባለ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል የሚሉት ወይዘሮ ውዴ በበኩላቸው «ጥያቄው የአርሶአደሩ፣ የሴቷ፣ የወጣቱና የነጋዴው ጥያቄ ነው» ብለዋል።

የመንግሥት  ምላሽ

ዶቼ ቬለ DW ሠልፈኞቹ ባቀረቡት አቤቱታ ዙሪያ የክልሉን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔንም ሆነ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ኃላፊዎቹ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ባለመሆናቸው አልተሳካም። ያምሆኖ አንድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ከፍተኛ ኃላፊ የሠልፈኞቹን ተወካዮች ተቀብለው አንዳነጋገሯቸው ከሠልፈኞቹ ተወካዮች አንዱ አቶ ፈለቀ አስፋው ገልጸዋል። «ጥያቄያችንን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰማን ሽፋ አቅርበናል» ያሉት አቶ ፈለቀ «ኃላፊውም ጥያቄያችን ቀደምሲል ጀምሮ ሲነሳ የነበረ መሆኑ አንደሚያውቁ ገልጸውልናል። የመዋቅር ጥያቄው አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲመሠረት አብሮ መልስ እንደሚያገኝ ነግረውናል» ብለዋል።

የሠልፈኞቹ ተወካዮች «በአራቱ ወረዳዎች እና በሦስቱ የከተማ አስተዳደሮች የምንገኝ ነዋሪዎች የፍትህና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት አደጋች ሆኖብን ቆይቷል» በማለት የጠቀሱት የሠልፈኞቹ ተወካዮች «የፍትህና ሌሎች አገልግሎቶችን ፍለጋ የዞኑ የአስተዳደር መቀመጫ ወደ ሆነችው ወልቂጤ ከተማ ድረስ ረጅም ኪሎሜትሮችን በመጓዝ ለእንግልትና ለወጪ ስንዳረግ ቆይተናል። አሁን ግን አገልግሎቱን በአቅራቢያችን የምናገኝበት ሁኔታ ሊመቻች ይገባል።» ብለዋል።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ተጨማሪ የአደረጃጀት ጥያቄዎች

በደቡቡ ክልል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቀረቡ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ላለፉት 30 ዓመታት የፌዴሬሽኑ አካል ሆኖ የቆየውን የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልን በአራት አዳዲስ ክልላዊ መስተዳድሮች እንዲዋቀር አስገድዶታል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በመደራጀት ላይ በሚገኙ ክልሎች ውስጥ ተጨማሪ የዞን መስተዳድርና የልዩ ወረዳ መዋቅር ጥያቄዎች እየቀረቡ ይገኛሉ። የአደረጃጀት ጥያቄውን እያቀረቡ ከሚገኙት መካከል በልዩ ወረዳ መዋቅር የቆዩት የአማሮ፣ የቡርጂ እና የደራሼ፣ ልዩ ወረዳዎች በዞን መዋቅር ለመደራጀት የጠየቁበት ይገኝበታል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW