1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ

እሑድ፣ ሚያዝያ 1 2015

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።

Äthiopien | Protest in Gurage
ምስል Tesfa G Nada

ሳምንታዊ የእንወያይ መሰናዶ

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ጥያቄው ሲነሳም መንግሥት ተገቢውን ሕገመንግሥታዊ ምላሽ እንደሚሰጥ አንቀጹ በግልጽ ይጠቅሳል ። ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ከዚህ ቀደም የሲዳማ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ባቀረቡት ጥያቄ ክልል ሆነዋል ። የጉራጌ ማኅበረሰብ በክልል እንደራጅ ጥያቄ ማቅረቡን ቀጥሏል ።

ጥያቄው ካለፉት ሦስት ዐሥርተ ዓመታት በላይ መዝለቁ ይነገራል ። የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ለአምስት ጊዜያት ከቤት ያለመውጣት አድማ አድርገው ጥያቄያቸው ምላሽ አላገኘም ። ይልቁንም አደባባይ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች በተተኮሱ ጥይቶች መገደላቸው እና በርካቶች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ዶይቸ ቬለ ከዚህ ቀደም ዘግቧል ። በተጨማሪም በክላስተር መደራጀትን በተመለከተ አንቀበልም ያሉ የጉራጌ ዞን እና የደቡብ ክልል የምክር ቤት አባላት፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሕግ ባለሞያዎች እንዲሁም ወጣቶች ለእስር መዳረጋቸው ተዘግቧል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ዞኑ በኮማንድ ፖስት ስር ከሆነ ወራት ተቆጥሯል ።

ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ጀሪካን ከፍ አድርገው ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት፦ ፎቶ ከማኅደርምስል privat

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወልቂጤ በሄዱበት ወቅት ነዋሪዎች ብርቱ ተቃውሟቸውን ከቤት ውስጥ ባለመውጣት ጭምር ገልጠዋል ።  ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?   ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? «የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ» ፦ የዛሬው የእንወያይ መሰናዶዋችን ርእሰ ጉዳይ ነው።

በውይይቱ 4 እንግዶች ተሳታፊ ናቸው። እንግዶቻችን 

  1. አብርሃም በርታ (/) የኢዜማ ፓርቲን በመወከል በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ተመራጭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል
  2. አቶ መላኩ ሣኅሌ፦ የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲፓርቲ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ
  3.  /ሮ ዛይዳ ግዛቸው፦ የወልቂጤ ከተማ ተወላጅ እና ነዋሪ የማኅበረሰብ አንቂ
  4. አቶ አሮን ዳጎል፦ የሕግ እና አስተዳደር መምሕር ናቸው

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW