1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች ሮሮ

ዓርብ፣ መስከረም 14 2014

በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግስት ወደ ቀድሞ ቀዬቸው ለመመለስ የገባውን ቃል ገቢራዊ ባለማደረጉ ለችግር ተዳርገናል አሉ። ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት እነኘሁ ተፈናቃዮች እስከአሁን ሲቀርብልን የነበረው የሰብአዊ የምግብ ድጋፍ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ በመቋረጡ ከነቤተሰቦቻችን በረሀብ ውስጥ እንገኛለን ብለዋል ።

Äthiopien Vertriebene in Guraferda
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

መንግስት ወደ ቀድሞ ቀዬቸው ለመመለስ የገባውን ቃል ገቢራዊ አላደረገም

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግስት ወደ ቀድሞ ቀዬቸው ለመመለስ የገባውን ቃል ገቢራዊ ባለማደረጉ ለችግር ተዳርገናል አሉ። ከአስራ አምስት ሺህ በላይ የሚሆኑት እነኘሁ ተፈናቃዮች እስከአሁን ሲቀርብልን የነበረው የሰብአዊ የምግብ ድጋፍ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ በመቋረጡ ከነቤተሰቦቻችን በረሀብ ውስጥ እንገኛለን ብለዋል።«ወይ ድጋፍ አላገኘን ወይ ወደ መንደራችን አልተመለስን እንዲሁ በመከራ ውስጥ እንገኛለን »ያሉት ነዋሪዎቹ መንግስት ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

አሁንም በከፊል ያልተመለሱ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ያረጋገጡት የወረዳው የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው በአካባቢው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባህላዊ የእርቅ ሥረዓቶችን በማድረግ ነዋሪዎቹን ወደ ቀደመ መንደራቸው የመመለሱ ስራ ግን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ለተፈናቃዮቹ የሰብአዊ የምግብ ድጋፍ ማቅረብ ያልተቻለው ወረዳው ለሚመለከታቸው የዞንና የክልል መስተዳደር ያቀረበው የድጋፍ ጥያቄ እስከሁን ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ብለዋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW