1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉሮሮ ካንሰር

እሑድ፣ ታኅሣሥ 14 2016

በውይይቱ ላይ በቀረበው ሪፖርት ጥናቱ ዳሰሳ ባደረገባቸው በ10 ሆስፒታሎች ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሞት እየፈጠሩ ካሉ የካንሰር አይነቶች መካከል ይህ የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር ሶስተኛው ነው።

Äthiopien Treffen zur Aufklärung über Kehlkopfkrebs in Addis Abeba
ምስል Hana Demisse/DW

የጉሮሮ ካንሰር

This browser does not support the audio element.

የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር በሽታ በአፍሪካ ሀገራት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሚታይ ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ በአብዛኛው በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና  ባሌ ዞኖች እንደዚሁም በሱማሌ ክልል አካባቤ ይታያል ። በኦሮሚያ ክልል ያሚገኙ 4 ዪንቨርስቲዎች ፣ አርሲ ዩንቨርስቲ ፣አርሲ ነገሌ ሆስፒታል ኮሌጅ ፣መደወላቡ ዪንቨርስቲ  እና አዳማ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ይህንን የ ምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር  በተመለከተ በቁጥር በተደገፍ   መረጃ  እና  ጥናት ተመስርተው  በሽታውን ለመከላከል ምን መደረግ እንዳለበት ከህክምና ባለሙያዎች  እና ከባለድርሻ አካላት ጋር  ውይይት አካሄደዋል ።በውይይቱ ላይ በቀረበው ሪፖርት ጥናቱ ዳሰሳ ባደረገባቸው በ10 ሆስፒታሎች ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሞት እየፈጠሩ ካሉ የካንሰር አይነቶች መካከል ይህ የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር ሶስተኛው ነው። በባሌ፣ አርሲ፣ ሰሜን ሻዋ በመሳሰሉት አካባቢዎች ደግሞ በስፋት እንደሚታይ በውይይቱ ተመልክቷል።   
 
በየአመቱ በኢትዮጵያ  ከ 77, 500  በላይ አዳዲስ የካንሰር በሽተኞች ይመዘገባሉ። ከማህፅን በር ካንሰር እና ከጡት ካንሰር ቀጥሎ የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል። የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር በሽታ  ባህሪ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንሳኤም ተጠንቶ ባለመታውቁ በሽታውን አስቀድሞ መከላከል አይቻልም መቀነስ ግን ይቻላል ሲሉ ለ DW የተናገሩት የካንሰር ስፔሽያሊስት ዶ/ር ማትዮስ አሰፋ  ናቸው።  
 
ከዳማ ዪንቪርስቲ ዶ/ር ሀጂ አማን  ‘’በፊት በእድሜ የገፉት ሰዎች ላይ ይከሰት የነበረውይህ ካንሰር አሁን በሰላሳዎቹ ላይ ባሉ ወጣቶችም ላይ መከሰት ጀምሮዋል።  አንድ ህመምተኛ የበሽታው ምልክቶችን መሰማት የሚጀምረው በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው። መጀመሪያ ምግብ መዋጥ ያቅተዋል፤  ከዛ ፍሳሽ መውሰድም ይሳነዋል፤   የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደኛ  ሲመጣ ተጎድቶ ነው ይላሉ ‘’ 
‘’በከፍተኛ ሁኔታ የዚህ ችግር የሚታይበት ክልል ኦሮሚያ ቤሆንም በሌሎችም  አካባቤዎች ችግሩን እያየን ለማህበረሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት ለመሰጠት ሲባል ሁሉም ክልል ውስጥ በተመሳሳይ ሊሰራ ይገባል። የኛ ሀገር ችግር ስላልተጠና ነው እንጂ እዚህ ይህን ያህል አዚያ ያን ያህል የምንልበት ጠንካራ የሆነ መረጃ የለንም ‘’ ሲሉ ለ DW የተናገሩት  የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል መንግስት  የጤና ቤሮ ሀላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ  ናቸው።  
በውይቱ ከተገኙት  መካከል ያነጋገርኩዋቸው ‘’እንዲህ አይነቱ ተንሳሽነት እጅግ የሚመሰገን  ይላሉ ነው።  ስለዚህ በሀገራችን በሁሉም ክልልሎች በተመሳሳይ ሊሰራ የሚገባው’’ ነው ይላሉ ። 
በማህበረሰቡ ዘንድ   የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰርን በሽታ  ምንንነት ለማሳወቅ  እና ግንዛቤ እንዲፍጥር ለማድረግ   አንባሳደር በመሆን የተሰየመችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስለህብረተሰባችን እና ስለሀገራችን ሁላችንም ያገባናል ብላለች ። 
በውይይቱ የተገኙት   የህክምና ባለሙያዎች፣ ዪንቨርስቲ እና ኮሌጆች፣ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት  እንደዚሁም የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ምክትል ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ሁሉም በሽታውን ለመከላከል እና ህመምተኞች በቂ ህክምና እንዲያገኙ የበኩላቸውን ለመድረግ  የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
ሃና ደምሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW