1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጋምቤላው ታታ ሐይቅ በእምቦጭ አረም መወረር

ዓርብ፣ የካቲት 25 2014

የታታ ሐይቅ 457 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን ጥልቀቱ በአማካይ 6 ሜትር እንደሚደርስ የጋምቤላ ክልል አካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ይገልጻል። የሐይቁ ግማሽ አካል በአረሙ የተሸፈነ ሲሆን ባህላዊ መንገድ አረሙን የመከላከል ሥራው መጀመሩንም ነዋሪዎች አመልክተዋል።

Äthiopien, Gambella | Menschen versuchen Wasserhyazinthe aus dem Lake Thatha zu entfernen
ምስል፦ Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office

የጋምቤላው ታታ ሐይቅ በእምቦጭ አረም መወረር

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ ክልል አኙዋ ዞን ጎግ ወረዳ የሚገኘው የታታ ሐይቅ በአንቦጭ አረም መወረሩን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት አስታወቁ። የሐይቁ ግማሽ አካል በአረሙ የተሸፈነ ሲሆን በባህላዊ መንገድ አረሙን የመከላከል ሥራው መጀመሩንም ነዋሪዎች አመልክተዋል። በዓሣ ማስገር የተሰማሩ ሰዎች ዓሣዎቹ በመጎዳታቸው ሥራቸውን እያቆሙ እንደሆነ ተገልጿል። የአንቦጭ አረም በአካባቢው በባሕላዊ መንገድ ለጨውነት ይዘጋጅ እንደነበር እና ይህን የማጠናከር ሥራ እንደሚሠራ ደግሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡ ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ዝርዝር ዘገባ አለው። 

የታታ ሐይቅ 457 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን ጥልቀቱ በአማካይ 6 ሜትር እንደሚደርስ የጋምቤላ ክልል አካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ይገልጻል።
ሐይቁ አሁን ባጋጠመው የእንቦጭ አረም ወረራ ምክንያት ግማሽ ያህሉ በእንቦጭ አረም ሲወረር ጥልቀቱም እየቀነሰ መምጣቱን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ተናግረዋል።
በሐይቁ ላይ የተፈጠረው የእንቦጭ አረም ከሐይቁ ዓሣ በማስገር የሚተዳደሩ ወገኖችን ያለሥራ እያስቀረ መሆኑን ደግሞ ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ሳሙኤል ኦቦያ ለዶቼ ቬለ አመልክተዋል፡፡
ሐየቁን ከጉዳት ለመከላከል በህዝብ ንቅናቄ በባሕላዊ መንገድ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የክልሉ አካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ገልፀዋል፡፡
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ዶ/ ኡጁሉ ኡኮክ በበኩላቸው ቀደም ሲል የአከባቢው ኅብረተሰብ አረሙን በባሕላዊ መንገድ ለጨውነት ይጠቀምበት ስለነበር ያንን ለማበረታታት እንደሚሠራና ሌሎች አረሙን የመከላከል ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል።
የእንቦጭ አረም ባህላዊ የመድኃኒትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዳለው ስለሚታወቅ ዩኒቨርሰቲያቸው በዚህ ዘርፍ የምርምር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶ/ር ኡጁሉ አብራረተዋል፡፡ሐይቁ የሚገኝበት የጎግ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቡላ ኡሪክ የወረዳውንና የሌሎች አጎራባች ወረዳዎች ነዋሪዎችን በማስተባበር ሐይቁን ከአጋጠመው የእንቦች አረም ለመታደግ እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አረሙ በጋምቤላ ክልል በሌሎች ውሀ አካላት ላይም እየተከሰተ መሆኑም ታወቋል።
ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW