1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልሎች የሠላም እና ልማት ትብብር መሰረቱ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2016

የጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልሎች የጋራ ፎረም መመስረታቸውን አስታወቁ፡፡ በተለይም የሙሪሌ ጎሳ ታጣቂዎች በወርቅ ማምረቻ አካባቢዎችና በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃችን ሲያደርሱ እንደነበር አመልክተዋል ።

የጋምቤላ ዋና ከተማ-ጋምቤላ
ጋምቤላ ከተማምስል Negassa Desalegn/DW

የጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልሎች የሠላም እና ልማት ትብብር

This browser does not support the audio element.

የጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልሎች የጋራ ፎረም መመስረታቸውን አስታወቁ፡፡ ሁለቱ ክልሎች የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በትናትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልል ቦንጋ ከተማ መመስረታቸውን ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎቸ  ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ መስል ጥቃቶችን በጋራ ለመከላከልና በልማት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የተመሰረተ ፎረም መሆኑንም የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎና የደቡብ ምዕራብ ክልል ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልን በሚያዋስኑ የጋምቤላ ክልል ዞኖችእንደ  ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ጎዳሬ ወረዳ እና በአኙዋ ብሔረሰብ ዞኖች ዲማ ወረዳ  አካባቢ በሙሪሌ ታጣቂዎች እና ስማቸው በውል ባልታወቁ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲደርስ እንደነበር ሁለቱ ክልሎች ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ስፍራዎች የሚገኙ ዞኖች ችግሩን ለመቅረፍ የጋራ የልማት ትብብር በማቋቋም ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ 
 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርማ ምስል South West Ethiopia People Region government Communication Affairs Bureau

የሙሪሌ ጎሳ ታጣቂዎችን ጥቃት መከላከል

የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ በትናንትናው ዕለት የተመሰረተ ፎረም በሰላም እና ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይም የሙሪሌ ጎሳታጣቂዎች በወርቅ ማምረቻ አካባቢዎችና  በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃችን ሲያደርሱ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ ይህንን መሰል ጥቃት በተቀናጀ መንገድ ለመከላልና አዋሳኝ ስፍራዎችን በልማት ለማስተሳሰር በትናንትናው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቦንጋ ከተማ የሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስዳድሮችና የፌደራል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሠላም እና የልማት ፎረም መመስረቱን አብራርተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ በበኩላቸው በአዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንዳይኖር እና ህግ ወጥ እንሰቅስቃሴዎች ለመከላከል በትብብር ለመስራት በስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም  የሁለቱ ክልሎች የሰላም እና ልማት ትብብር  ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ለማድርግ ታስቦ የተመሰረተ ፎረም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ  የኢንቨስትመንት ስራዎችና የንግድ እንቅስቃሴን ከስጋት ነጻ ለማድረግ የጋራ ሠላም እና የልማት ትብብር ስራዎች ወሳኝ እንደሆኑም አመልክተዋል።   

ኦሞድ ኦጁሉ-የጋምቤላ ክልል ርዕስ መስተዳድርምስል Gambella Communication

በጋምቤላ  እና በደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም አንስቶ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሰዋል፡፡ በሁለቱ ክልሎች አወሳኝ ስፍራዎች የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ሲባል  በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ከጋምቤላ ክልል እንደ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን እና ማጃንግ ዞን እንዲሁም  ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ደግሞ ቤንቺ ሸኮና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በሠላም ጉዳዮች በትብብር ለስመስራት በሐምሌ 4/2015 ዓ.ም በዲማ ወረዳ  ውይይት አካሂዶ ነበር፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW