1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጋምቤላ ክልል ከ40 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገባ

ረቡዕ፣ ግንቦት 27 2017

የወርቅ ምርት የሚገኝባቸውን አካባቢዎች የሰላም ችግር በመፈታቱ እንዲሁም ለአምራቾች የሚከፈለው ዋጋ በመጨመሩ ወደ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን መጨመሩን አብራርተዋል፡፡ በክልሉ በ2016 ሶስት ኩንታል ገደማ ወርቅ ወደ ባንክ መግባቱን ተገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሲያደርግ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲሕ የዘንድሮዉ በጣም ከፍተኛዉ መሆኑ ተነግሯል።
የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ የጋምቤላ አደባባይ።በወርቅ ማዕድን ምርት ከሚታወቁት የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ የሆነዉ ጋምቤላ ዘንድሮ ከ40 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሒራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን አስታዉቋልምስል፦ Negassa Desalegn/DW

የጋምቤላ ክልል ከ40 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገባ

This browser does not support the audio element.


በጋምቤላ ክልል ከሶስት ዓመት ወዲህ ከፍተኛ የተባለው የወርቅ መጠንወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱ ተገልጸዋል፡፡ጋምቤላ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ከሚገኝባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች አንዱ ነዉ።የክልሉ የማዕድን ልማት ቢሮ እንዳስታወቀዉ ዘንድሮ  ከ4ሺ 2 መቶ ኪሎ ግራም  በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ገብቷል።የጋምቤላ ክልል የማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ኡጁሉ ጊሎ እንዳሉት አብዛኛዉ ወርቅ የተመረተዉ ከክልሉ ማጃንግና አኙዋ ዞኞች ነዉ።የኢትዮጵያ የማዕድን ሐብት አመራረት ከባሕላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ አመራረት መለወጥ እንዳለበት የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች ይመክራሉ።የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ከጋምቤላ ከ4ሺ በላይ ኪ.ግ ወርቅ ወደ ባንክ ገብቷል
በጋምቤላ ክልል በአሁኑ ወቅት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በወርቅ ምርት እየተሳተፉ እንደሚገኙ የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አመልክተዋል፡፡  በክልሉ ዲማ ወረዳ፣ጎግ፣አቦቦ እና ሌሎች ወረዳዎች ወርቅ በብዛት የሚገኝባቸው እና እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ  ከእያንዳንዳቸው ወደ ባንክ መግባቱን  ተገልጸዋል፡፡ 
በጋምቤላ እስካሁን ከ40 ኩንታል በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በህገ ወጥ መንገድ ወርቅ በመሸጡ ወደ ባንክ ይገባ የነበረው የወርቅ መጠን ቀንሶ እንደ ነበር የተናገሩት ኃላፊ የወርቅ ምርት የሚገኝባቸውን አካባቢዎች የሰላም ችግር በመፈታቱ እንዲሁም ለአምራቾች የሚከፈለው ዋጋ በመጨመሩ ወደ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን መጨመሩን አብራርተዋል፡፡ በክልሉ በ2016 ሶስት ኩንታል ገደማ ወርቅ ወደ ባንክ መግባቱን ተገልጸዋል፡፡
‹‹የማዕድን ዘርፍ አሰራሩ መዘመን አለበት››
በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገሮች መሰረታቸው የማዕድን ሀብት እና ሌሎችን የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት እንደሆነ የሚናገሩት የምጣኔ ሀብት ምሁራን ኢትዮጵያውድና ዘርፈ ብዙ ማዕድናት ያሏት ቢትሆንም የአመራረት ዜደው ባህላዊ በመሆኑ የሀገሪቱን  ኢኮኖሚ ከማሳደግ አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት ምሁር የሆኑት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ  በማዕድን ዘፍር በተለይም የወርቅ ምርት ላይ ይስተዋሉ ከነበሩት ችግሮችን አንዱ ለአምራቾች የሚከፈው ገዘንብ አነስተኛ መሆን፣ ወርቅ በኮንትሮባንድ መልኩ እንዲሸጥ ከፍተኛ ሚና እንደነበር አመልክተዋል፡፡ በተጨማሪም  አሰራሩ ባለመዘመሩ አብዛኛው አሁን በባህላዊ ዜዴ የሚሠራ በመሆኑ በምርቱ መጠን ላይ ተጽህኖ እንዳለው በመግለጽ ለወርቅ አምራቾች የተደረጉ የዋጋ ማሻሻዎች ምርቱ ወደ ባንክ እንዲመጣ አድርጓል ብሏል፡፡ 

የኢትዮጵያ የወርቅም ሆነ የሌሎች ማዕድናት አመራረት ከባሕላዊዉ የምርት ዘዴ ወደ ዘመናዊዉ ሥልት መለወጥ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመክራሉምስል፦ Ujulu Gilo

በተለይም በአፍርካ እንደ ደቡብ አፍርካ፣ቦትስዋና፣ እና ናይጀርያ ያሉ ሀገሮች የማዕድን ዘርፍ አሰራር  መዘመኑን እና  የየሀገራቱን ዕድት እየጨመረ እንደመገኝ በማንሳት በኢትዩጵያም የከበሩ ማዕድናት የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በመለየት፣ በጥናትና በዘመናዊ መንገድ በማልማት የሀገርቷን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበሩት አሰራሮች ወርቅ ከኢትዮጰያ በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ሱዳን እና  በኬኒያ በኩል ይሸጥ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ጉቱ ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀነሱን አንስተዋል፡፡
 በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችበዚህ ዓመት እስካሁን ከ70 ኩንታል በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንካ መግባቱን ተገልጸዋል፡፡ በጋምቤላ በ2015 እና 16 ወደ ብሔራዊ ባንክ የገቡ ወርቅ መጠን ከ1ሺ ኪ.ግ በታች እንደነበር እና በጣም አነስተኛ እንደነበር ከዚህ ቀደም ተዘግበዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ    
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW