1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋናው ፕሬዝዳንት አረፉ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 2004

የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ኤቫንስ አታ ሚልስ ዛሬ በድንገት አረፉ። የ68 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ሚልስ ሲታከሙ በነበረበት ወታደራዊ ሆስፒታል ዛሬ ማረፋቸውን መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። መንግሥት እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሰአት በኋላ ህክምና እንዲደርግላቸው

President of Ghana, John Evans Atta Mills, addresses the 66th session of the United Nations General Assembly, Friday, Sept. 23, 2011. (ddp images/AP Photo/Richard Drew)
ምስል AP

የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ኤቫንስ አታ ሚልስ ዛሬ በድንገት አረፉ። የ68 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ሚልስ ሲታከሙ በነበረበት ወታደራዊ ሆስፒታል ዛሬ ማረፋቸውን መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። መንግሥት እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሰአት በኋላ ህክምና እንዲደርግላቸው በገቡበት በ37 ተኛው ወታደራዊ ሆስፒታል በመታከም ላይ ሳሉ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቀደም ሲል ትናንት ምሽት ህመም እንደተሰማቸው ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ረዳታቸው

ምስል dapd

አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ሚልስ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ታክመው ነበር። ዛሬ ግን የፕሬዝዳንቱን ሞት በልባዊና ጥልቅ ሃዘን እናስታውቃለን ሲል መንግሥት በመግለጫው ማስታወቁ ተዘግቧል። ሚልስ እጎአ በ2008 መጨረሻ ላይ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጠባብ ሉዩነት አሸንፈው በ2009 ዓም መጀመሪያ ላይ ነበር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ኩፎርን በመተካት የጋና ፕሬዝዳትነት ሆነው ሥልጣን የያዙት። ፕሬዝዳንት ሚልስ በሚቀጥለው ዓመት በታህሳስ ወር ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በገዥው የብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ምክር ቤት በእጩ ፕሬዝዳንትት ተሰይመው ነበር።

ምስል AP

የጋናው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ዛሬ ማምሻውን ለፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ ሮይተርስ ከመዲናይቱ አክራ ዘግቧል። በጋና ህገ መንግሥት መሠረት ማሃማ ታህሳስ ወር በሚካሄደው ምርጫ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት እስኪወሰን ድረስ የሚልስን የሥልጣን ዘመን እስኪጠናቀቅ ሃገሪቱን ይመራሉ። 

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW