1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዛው ጦርነት ተጽእኖ ያደረገበት የፓሪሱ የፈረንሳይና የእስራኤል ብሔራዊ ቡድኖች ግጥሚያ

ዓርብ፣ ኅዳር 6 2017

የትናንቱ የፓሪሱ ግጥሚያ በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ነበር የተካሄደው። ወደ 4ሺህ የሚጠጋ ፖሊስና የፈረንሳይ የፀጥታ ኃይሎች በስታድዮሙ ውስጥና ከስታድዮሙ ውጭ ቢሰማራም ግጥሚያው በተካሄደበት እስከ 80ሺህ ተመልካች በሚይዘው በስታድ ደ ፍራንስ ስታድዮም ትናንት የተገኘው 16,611 ነበር።

Fußball Nations League | Frankreich - Israel
ምስል Fred Dugit/LE PARISIEN/MAXPPP/dpa/picture alliance

የጋዛው ጦርነት ተጽእኖ ያደረገበት የፓሪሱ የፈረንሳይና የእስራኤል ብሔራዊ ቡድኖች ግጥሚያ

This browser does not support the audio element.

በፈረንሳይና በእሥራኤል ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል ውጥረት በሰፈነበት ሁኔታ ፓሪስ ውስጥ ትናንት ምሽት በተካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ላይ በተፈጠረ ረብሻ መንስኤ ፖሊስ 40 ሰዎች ማሰሩን አሰታውቋል። የእስራኤሉ ክለብ የማካቢ ቴላቪቭ  ደጋፊዎች ከአንድ ሳምንት በፊት አምስተርዳም ኔዘርላንድ ውስጥ ከደረሰባቸው ድብደባ በኋላ የትናንቱ የፓሪሱ ግጥሚያ በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ነበር የተካሄደው።የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ቁጥሩ ወደ 4ሺህ የሚጠጋ ፖሊስ እና የፈረንሳይ የፀጥታ ኅይሎች በስታድዮሙ ውስጥና ከስታድዮሙ ውጭ ተሰማርቶ ነበር።ይህ ሁሉ ዝግጅት ቢደረግም ግጥሚያው በተካሄደበት እስከ 80ሺህ ተመልካች በሚይዘው በስታድ ደ ፍራንስ ስታድዮም ትናንት የተገኘው 16,611 ነበር።

የአትሌት አበበ ቢቂላናደራርቱ ቱሉ መታሰቢያ ዝግጅት በፈረንሳይ

ስለ ትናንት ምሽቱ የፓሪሱ እግር ኳስ ግጥሚያና በስታድዮሙና ከስታድዮሙ ውጭ ስለነበሩ ክስተቶች የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሪያታለሁ ሃይማኖት የስታድዮሙ ድባብ ምን ይመስል እንደነበር በመግለጽ ትጀምራለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW