1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዛ ቀዉስ እና የአዉሮጳ ሕብረት ሚንስትሮች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2016

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የጋዛ ሕዝብ ርዳታ ይደርሰዉ ዘንድ እስራኤል ላጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ፋታ እንድታደረግ ለመጠየቅ በቀረበዉ ሐሳብ ላይ ሳይስማሙ ቀሩ። የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ገሚሶቹ «የሰብአዊ ርዳታ ፋታ» እንዲደረግ ሲደግፉ ሌሎቹ ግን እስራኤል ጋዛን መደብደቧን እንዳታቋርጥ ተሟግተዋል።

የአዉሮጳ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ
የአዉሮጳ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ምስል Virginia Mayo/AP Photo/picture alliance

በመካከለኛዉ ምስራቅ በቀጠለው ቀዉስ ላይ ለመነጋገር የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች በመጪዉ ሳምንት ይሰበሰባሉ

This browser does not support the audio element.

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የጋዛ ሕዝብ ርዳታ ይደርሰዉ ዘንድ እስራኤል ላጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ፋታ እንድታደረግ ለመጠየቅ በቀረበዉ  ሐሳብ ላይ ሳይስማሙ ቀሩ።

በጋዛ የቀጠለው ግጭት እንዲቆም የጠየቀው የብራስልስ ሰልፍትናንት ከተሰበሰቡት የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ገሚሶቹ «የሰብአዊ ርዳታ ፋታ» እንዲደረግ ሲደግፉ ሌሎቹ ግን እስራኤል ጋዛን መደብደቧን እንዳታቋርጥ ተሟግተዋል። ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በተከፋፈሉበት ሐሳብ ላይ የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች በመጪዉ አርብ ይነጋገሩበታል ተብሏል።

ዛሬ ቴል አቪቭን የጎበኙት የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ ላጭር ጊዜ ተኩስ እንዲቆም የሚጠይቀዉን ሐሳብ ይደግፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ነጋሽ መሐመድ

ገበያዉ ንጉሴ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW