1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጋዜጠኝነት ገጽታ በአፍሪቃ እና የሰብዓዊ ቀውስ በምስራቃዊ ኮንጎ

ፀሀይ ጫኔ
ቅዳሜ፣ የካቲት 1 2017

በአፍሪቃ የጋዜጠኝነት ገፅታ ሲታይ በሰዎች ታሪክ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ዜናዎች 7 በመቶ ብቻ ናቸው።ቀሪዎቹ 87 በመቶ ዜናዎች ፖለቲካን በመሳሰሉ ጠንካራ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በሌላ በኩል በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል የ የኤም23 አማፂያን የማዕድን ማውጫ አካባቢን ከተቆጣጠሩ ወዲህ፤በአካባቢው የሰብዓዊ ቀውስ ጨምሯል።

Demokratische Republik Kongo M23-Rebellen
ምስል፦ Moses Sawasawa/AP Photo/picture alliance

ትኩረት በአፍሪቃ፤የጋዜጠኝነት ገጽታ በአፍሪቃ እና የሰብዓዊ ቀውስ በምስራቃዊ ኮንጎ

This browser does not support the audio element.

በሰዎች ታሪክ ላይ ካተኮሩ ዜናዎች ይልቅ የጠጣር ዜናዎች መብዛት፣ለተለያዩ ድምጾች የሚሰጠው ቦታ ማነስ  እና የዲጂታል ዘገባዎች እንደ እጉዳይ ቢፈሉም ጥራት የሌላቸው ዘገባዎች መበራከት ባለሙያዎች እንደሚሉት በአፍሪቃ አህጉር  የሚታዩ የጋዜጠኝነት ችግሮች ናቸው።
እንደ ናታሻ ኪማኒ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ተመራማሪዎች ከ/አፍሪካ ኖ ፊልተር/  ይህ የጋዜጠኝነት ሁኔታ ሊሻሻል የሚችልበት መንገድ አለ ብለው ያስባሉ። -
 አፍሪካ ኖ ፊልተር የተባለው የናታሻ ኪማኒ  ድርጅት በአህጉሪቱ 81 % ዜናዎች ጠጣር ዜናዎች ሲሆኑ 7 በመቶው ብቻ የሰው ታሪኮች እንደሆኑ አመልክቷል። ነገር ግን እንደ ቱላናና ቦሄላ (ኦና ስቶሪስ) እና ናታሻ ኪማኒ ያሉ ወጣት የመገናኛ ብዙሃን አዘጋጆች በአፍሪካ አህጉር የወደፊት የጋዜጠኝነት ስራ ምን ሊመስል እንደሚችል አዳዲስ ሀሳቦች አሏቸው።
ያ የታንዛኒያ የመገናኛ ብዙኃንስራ ፈጣሪ ቱላናና ቦሄላ በአፍሪካ የወደፊት የጋዜጠኝነት ስራ ላይ ገለጻ እያደረገች ነው። እሷ እንደምትለው «ታሪክ ነገራ  የሰው ልጅ  የሚወደው  በተፈጥሯዊ ነገር ነው። የሰው ልጆች ዓለምን ለመረዳት ተረት ተረት ይጠቀማሉ."
በገለጻ ዋ ወቅትም ከስክሪኑ ላይ ሁለት ጽሑፎችን ታነባለች። ከጽሁፎቹ አንዱ በማሽን የተፃፈ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሰው የተፃፈ ነበር።ቦሄላ ተሰብሳቢዎቹን ማን ምን እንደፃፈ መገመት ይችሉ እንደሁ ትጠይቃለች።ስብሰባው  በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተሞላ ነው።- ግን ማንም ልዩነቱን ሊያውቅ አልቻለም።

ሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለዜና ስራ

በሰው ሰራሽ አስተውሎት  ቴክኖሎጂ የመገናኛ ብዙሃን ዜናዎችን መስራት መጀመራቸውን የምትገልፀው የመገናኛ ብዙሃን የስራ ፈጣሪዋ ቦሄላ፤ አፍሪቃ እንደ አህጉር  ወደ ኋላ መቅረት የለባትም ትላለች። የአፍሪካ ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂን በዜና ክፍላቸው ውስጥ ለመጠቀም ከዘገዩ፣ ምርቶች በምዕራባዊ ወገንተኝነት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነውም ትላለች።
«ዛሬ ጊዜው  አደገኛ ነው።ለምሳሌ አፍሪካን በ 360 የሚል ቪዲዮ በ ዩቲዩብ ላይ ሳስቀምጥ, የሚመጣው የዝሆኖች ምስል ነው። ታውቃላችሁ! የዝሆኖች ምስል! ስለዚህ አሁን እነዚህን የምስል ክምችቶች እና  ይዘቶች በመፍጠር  ፣360 ቪዲዮዎችን በማከማቸት፣እንዲሁም ሁሉንም ነገር በማካተት እነዚህን ክፍተቶች  መሙላት  አሁን የእኛ ፋንታ ነው።»
ቦሄላ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመሞከር  እና ለመለማመድ እድሉ ያስፈልጋቸዋል ብላ ታምናለች። ለዚህም ነው ከሁለት አመት በፊት የራሷን የመገናኛ ብዙሃን ድርጅት  በታንዛኒያ የመሰረተችው። «ኦናአ ኬሾአ» ይባላል።
«እኛ መድረክ እናመቻቻለን።  የመጫወቻ ሜዳ ፣ የመጫወቻ ሜዳ ብለን እንጠራዋለን። ታሪክ ነጋሪዎች መጥተው እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ማግኘት እንዲችሉ። ስለዚህ፣ምናባዊ እውነታ  የሚሆኑ ዲጅታል ቁሳቁሶች እንደ ፣የጆሮ ማዳመጫዎች፣ ካሜራ፣ ኤአር፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፣ እነዚህን ሁሉ ታሪካቸውን ለመንገር  ሊጠቀሙበት ይችላሉ።»

 የአፍሪካ የዜና ማሰራጫዎች ጠንካራ ዜናዎች ላይ ያተኩራሉ

ቱላናና ቦሄላ እንደምትለው የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎችማለት በአዳዲስ  ቅርጸች ብቻ መጫወት አይደለም።ይልቁኑ ለአዳዲስ ታዳሚዎች አዳዲስ ታሪኮችን ለማግኘት የሚረዳ ነው።«ዲጂታል መገናኛ ዘዴ  እንደ እንጉዳይ ነው።  እናም በአህጉሪቱ ውስጥ እያደገ ነው።ይህም ሰዎች እኛ የማንሰማውን ታሪካቸውን እንዲናገሩ ብዙ ሃይል እና  ውክልና ተሰጥቷቸዋል።« በማለት ገልጻለች።
«ዲጂታል ሚዲያ እንጉዳይ ነው እናም በአህጉሪቱ ውስጥ እያደገ ነው። ሰዎች እኛ የማንሰማውን ታሪካቸውን እንዲናገሩ ብዙ ሃይል እና ኤጀንሲ ተሰጥቷቸዋል።»ብላለች።

ነገር ግን አብዛኞቹ የአፍሪካ የዜና ማሰራጫዎች በዚያ ላይ ያተኮሩ ታሪኮች   አይደሉም። ይልቁንም ከባድ ዜናዎችን ያሰራጫሉ።. ይህ ማለት ዘገባ በሚደረግባቸው ክስተቶች የተጎዱ ሰዎች ብዙ ጊዜ አይሰሙም ወይም አይታዩም። የናታሻ ኪማኒ «አፍሪካ ኖ ፊልተር» የተባለ  ድርጅት አላት።ድርጅቷ ያንን መለወጥ ይፈልጋል።የድርጅቱ ተመራማሪ ናታሻ የጋዜጠኝነት ስራ በአፍሪካ የሚኖረውን የወደፊት  ፅታ እንዲህ  ትገልፃለች።
«የበለጠ ብዝሃነት፣ የበለጠ የሰዎች ታሪክ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በአፍሪካ ውስጥ ከተዘገቡት ታሪኮች ውስጥ 7 በመቶው ብቻ የሰዎች ታሪኮች ናቸው። 81 % ጠጣር ታሪኮች ናቸው። የተለያዩ ድምፆችን እና የተገለሉ ድምፆችን አያጎሉም። በተገለሉ የማህበረሰብ፣ ክፍሎች ውስጥ ያሉ ግብረሰዶማውያን ሴቶች እና ወጣቶችም ታሪካቸው አይነገርም። »ብላለች።

ሰብዓዊ ቀውስ በምስራቃዊ ኮንጎ

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎምስራቃዊ ክፍል የምትገኘው እና የአንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ የሆነችው የጎማ ከተማ  ኤም 23 ሚሊሻን ጨምሮ የአማፂ ጥምረት በጥር ወር መጨረሻ  ወደ ከተማይቱ ከገሰገሱ ወዲህ ነዋሪዎቿ አስጨናቂ ጊዜን አሳልፈዋል። ከቀናት ጦርነት በኋላ አማፂያኑ ጎማን ተቆጣጥረው ነበር። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጦርነቱ 900 ሰዎች ተገድለዋል።

የኤም23 አማፅያን በከፈቱት በጦርነት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።የተጎዱ በርካታ ሰዎችን ለማከም ሆስፒታሎች ከአቅማቸው በላይ ሆኗል።ምስል፦ Alexis Huguet/AFP/Getty Images

በከተማዋ በአብዛኛው የመኖሪያ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው መብራት እና ውሃ  ተመልሷል። የመብራት እና ውሃ መመለስ  ግን የከተማዋን የሰብዓዊ ሁኔታ ለማረጋጋት በቂ አይደሉም። DW መሬት ላይ እንደተረዳው።የከተማዋ ተግዳሮቶች የበሽታ ከመስፋፋትን እና በርካታ አስከሬኖችን መቅበርን ያጠቃልላል። በተጨማሪም ሆስፒታሎች ከሚችሉት አቅም በላይ ሆኖባቸዋል።ምክንያቱም ከመደበኛ ቀዶ ጥገና በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ የተጎዱ ሰዎችም መታከም አለባቸው።
DW 146 አልጋዎች ያሉት ቀይ መስቀል ሆስፒታል 290 ህሙማንን ጎብኝቷል። ባለ አንድ ፎቅ ህንጻ ባለበት ቦታ ላይ ተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሚያስተናግዱ ነጭ ድንኳኖች ተጥለዋል።በጎማ ቀይ መስቀል ሆስፒታል ለመታከም ታካሚዎች በፕላስቲክ ወንበሮች ይጠበቃሉ።
የድንገተኛ ክፍል ዶክተር አብዱራማን ሲዲቤ ሁኔታውን እንዲህ ያስረዳሉ።
 «በአሁኑ ጊዜ የፍጆታ እቃዎች እና መድሃኒቶች ማለትም,ህክምናን ለማቅረብ የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ እንፈልጋለን።. እንደሚታወቀው የእኛ መጋዘን ተዘርፏል።ይህም ህክምናን አስቸጋሪ ያደርገዋል።  ከአጋሮቻችንን መድሃኒት ጠይቀን ነበር። ነገር ግን ዘግይተዋል። አሥር ቀናት አለፈ።ይህ ስራችንን ከባድ ያደርገዋል።»

የኤም 23 አማፅያን የተኩስ አቁም እና የመንግስት ጥርጣሬ 

ያለፈው ማክሰኞ፣ አንድ ወገን የሆነ ሰብአዊ የተኩስ አቁምተግባራዊ ሆኗል። በኤም 23 የሚመራው ጥምር የእርቅ ስምምነት ይፋ መሆን ፤ቢያንስ ለጊዜው ውጥረቱን ለማርገብ ይረዳ እንደሁ ግን ለማወቅ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም።  በሩዋንዳ የሚደገፈው ኤም 23 ሌሎች አካባቢዎችን ለመያዝ ምንም አላማ እንደሌለው አስታውቋል።
ነገር ግን የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰራዊትም ሆነ መንግስት ጥርጣሬ  አላቸው።የመንግስት ጦር ቃል አቀባይ ሲልቫን ኤኬንጌ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ ከክልሉ ዋና ከተማ ቡካቩ 100 ኪሎ ሜትር (60 ማይል) ርቃ የምትገኘውን የደቡብ ኪቩ ማዕድን ማውጫ ከተማን ኒያቢብዌን የተቆጣጠሩት የኤም 23 ተዋጊዎች፤ ሁልጊዜ ከሚናገሩት ተቃራኒ ነው ። መንግስት እንደሚለው አማፂያኑ የተኩስ አቁም ጥሪው ራሳቸውን እንደገና ለማደራጄት ሊሆን ይችላልም ይላሉ።
በደቡብ አፍሪካ የደህንነት ጥናቶች ተቋም   (አይኤስኤስ)  ባለሙያ ስቴፋኒ ዎልተርስ የተኩስ አቁም መታወጁ ጥቅም አለው ባይ ናቸው። 
«በእኔ ዕይታ  ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ M23 ብዙ ትችቶች ደርሶባቸዋል።እና የተኩስ አቁም መታወጁ ጥሩ ይመስላል። ለመደራደር ወይም ግጭቶችን ለማስቆም ወይም የሰብአዊ ዕርዳታ እንደገና እንዲቀጥል ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ ይመስላል።»

የችግር ጊዜዎች እና የጦርነት ፍርሃት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች ባለሙያዎች እንደሚሉት ሩዋንዳ M23 ን በሎጂስቲክስ፣ አልፎ ተርፎም በወታደራዊ ጉዳዮች በንቃት ትደግፋለች። የኪጋሊ  መንግስት እነዚህን ዘገባዎች ውድቅ ያደርጋል። በ1994 በሩዋንዳ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የሁቱ አባላት በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ቱትሲዎች፤ በM23 ተዋጊዎች ውስጥ በብዛት እንደሚገኙም ይነገራል።
ሆኖም ግን አሁን ያለው ሁኔታ በኪጋሊ እና በኪንሻሳ እንደሚነገረው ሳይሆን፣ ተባብሶ  ወደ ሌላ ትልቅ ጦርነት ሊመራ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል። እንደ ዘገባው ከሆነ ኡጋንዳ በምስራቅ ኮንጎ ያላትን ወታደራዊ ይዞታ በ1,000 ወታደሮች ጨምራለች። አሁን ያለው ጦርም በድምሩ ከ4,000 እስከ 5,000  ይደርሳል።  በጎርጎሪያኑ 1996 እና በ 2003 መካከል በማዕድን የበለፀገው ክልል ብዙ የታጠቁ ቡድኖችን ያካተቱ ሁለት ጦርነቶችን ተከሂደውበታል።፣ በነዚህ ጦርነቶችም ስድስት  ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በኮንጎ ጎማ ከተማ ፤ሆስፒታሎች ከመደበኛ ስራቸው በተጨማሪ በሰሞኑ ግጭት የተጎዱ ሰዎችን ያክማሉ። ነገር ግን የመድሃኒት እጥረት ፈተና ለጤና ተቋማቱ ሆኗል።ምስል፦ DW

ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለእርዳታ ስራ

ሁለተኛው የኮንጎ ጦርነት ካበቃ  ከ20 ዓመታት በላይ  ሆኖታል። እነዚህ አመታት አለመረጋጋት የታየባቸው ነበሩ። ከውጊያ በተጨማሪ በተለያዩ ታጣቂዎች  ዝርፊያ  እና አሰገድዶ መድፈር መፈፀሙ፤ ሰዎች ደጋግመው እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል። ተባብሶ ከቀጠለው ከቅርብ ጊዜው ግጭት በፊትም  በሰሜን እና ደቡብ ኪቩ ችግር በተከሰተባቸው ግዛቶች 4.6 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ገልጿል።
ስለሆነም በአካባቢው ለሰብአዊ እርዳታ ደህንነቱ የተጠበቀ የመተላለፊያ መንገድ ያስፈልጋል ይላሉ።የዩኤን ኤች ሲ አር ቃል አቀባይ ኢዩጂን ቢዩን ።
«እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ተደራሽነት ነው።ለሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እና  በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ መንገድ ነው። መንገዱ ዝግ መሆኑን እና  በአካባቢው ለሚዘዋወሩ ሰዎች ደህንነት አስቸጋሪ መሆኑን እየሰማን ነው።  ለዚያም ነው ለሰብዓዊ እርዳታም ሆነ ለተቸገሩ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመተላለፊያ መንገድ የምንጠይቀው ።»ብለዋል።
ያምሆኖ ሃላፊዋ  እንደሚሉት በጎረቤት ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የስደተኞች ፍልሰት እየታዬ አይደለም።«ማስታወስ አለብን።ቀደም ሲል በምስራቅ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ሰዎች በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል ። ስለዚህ በአጎራባች አገሮች ውስጥ ጉልህ የሆነ መፈናቀል እያየን አይደለም።ምክንያቱም በአገራቸው መቆየት ስለሚሹ ድንበር መሻገር አይፈልጉም። ።»በማለት አስረድተዋል።

ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው እንዳይሰደዱ መከላከል

ስለሆነም በዚህ ጊዜ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ድንበር አቋርጠው ለመሰደድ  እንዲወስኑ የሚያደርግ  ጫናን መከላከል  አስፈላጊ  ነው ብለዋል።
ኤም 23 እና አጋሮቹ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ካበቃ በኋላ ግስጋሴያቸውን ከቀጠሉ  በደቡብ ኪቩ ግዛት ብዙ ሰዎች ሊሸሹ ይችላሉ።የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከመታወጁ በፊት ዶቼ ቬለ  ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ ስጋታቸውን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል።
«ጎማ ከቡካቩ ብዙም አይርቅም። ሰዎች ወደ ውጭ ሳይወጡ ሶስት ቀናት እንቆዩ ታውቃላችሁ።እዚህ ቡካቩ ውስጥ አንድ ቀን  ከእንቅልፋችን ስንነቃ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገባለን ብለን እንሰጋለን።»ብለዋል።

በመሆኑም እኚህ ነዋሪ ድንበር አቋርጠው ወደ ቡሩንዲ መሸሽ ፈልገዋል።ከዚህ አንፃር የኤም23  ሚሊሻዎችወደ ቡካቩ ከገፋ፣ አንድ ሚሊዮን የከተማዋ ነዋሪዎች ተመሳሳይ ውሳኔ ሊወስኑ ይችላሉ።
ሁኔታው ያሳሰበው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል ባለፈው አርብ በጄኔቫ ባደረገው ስብሰባ በግጭቱ ውስጥ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት ውሳኔ ሰጥቷል።የመንግስታቱ ድርጅት የመብት ሃላፊ ቮልከር ቱርክ “በክፍለ አህጉሩ እየሰፋ የሄደው የግጭት አደጋ ከፍ እያለ እንደሚሄድ አስጠንቅቀዋል።
ይህ ግጭት መፍትሄ ካለጋኘም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚኖሩ ሕዝቦች ብቻ ሳይሆን ከአገሪቱ ድንበሮች በላይ የከፋ ነገር ሊመጣ ይችላልም ብለዋል።ቱርክ እንዳሉት ኤም 23 አማፅያን ከጎርጎሪያኑ ጥር 26 ቀን 2025 ወደ ጎማ ከገቡ ወዲህ ወደ 3,000 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን እና 2,880 ቆስለዋል።ግጭቱ ካልቆመ ጉዳቱ ምናልባት ከዚህ የበለጠ ሊሆን እንደሚችልም ሀላፊው አስጠንቅቀዋል።


ፀሀይ ጫኔ
ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW