1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች መታሰር

ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2015

የአራት ኪሎ ሚዲያ መስራች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ጋዚጠኛ አላዛር ተረፈ የሙያ አጋሩ የሆነው ጋዚጠኛ ዳዊት በጋሻው በመንግስት ሀይሎች የተያዘዉ ባሕር ዳር ዉስጥ መሆኑን አስታዉቋል።

Symbolbild Exil-Journalismus/Schutz von gefährdeten Journalist*innen | Belarus
ምስል Aleksander Kalka/ZUMA Wire/picture alliance

6 የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች ተይዘዋል

This browser does not support the audio element.


የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን ያለ በቂ ምክንያት ማሰሩን እንዲያቆም የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች ማሕበር ጠቀየ።የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ዉስጥ ብቻ 6 ጋዜጠኞች፣የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ሰራተኞችና አቀንቃኞችን አስሯል።የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች ማሕበር ኃላፊ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ እንደሚለዉ ጋዜጠኞች ሥራቸዉን በነፃነት የመከወን መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባል።ሐና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች,
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር መንግስት በመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች  ላይ  የሚያደርሰውን  እስር እና  እንግልት ያቁም ሲል ተደጋጋሚ መግለጫ ያወጣል። ያም ሆኖ የጋዚጠኞች በነጻነት የመስራት መብት  ከድጡ ወደማጡ እየሆነ ከመጣ ሰነበብቶዋል።  በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ በፋና ራዲዮና ቲሌቪሽን እና በሌሎችም ሚዲያዎች በመስራት ለሙያው ታማኘ የሆነውን ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ ፣ አራጋው ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ፣ጌትነት አሻግሬ፣ በየነ ወልዴ ፣ቴዎድሮስ አስፋው እና መስከረም አበራ  ባለፉት ሳምንታት በመንግስት ሀይል በቁጥጥር ስል የዋሉ የሚዲያ ባለሙያዎች ናቸው።
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር ሀላፊ  ጋዚጠኛ ጥበቡ በለጠ ጋዜጠኞች ቢያንስ የአካል ነፃነት አግኝተው ጉዳያቸውን መከታተል እንዲችሉ መንግስት መፍቀድ አእለበት ሲል ለ DW ተናግሯል። 
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በአንድ ሀገር ውስጥ ለዲሞክራሲ እድገት ወሳኝ ከመሆናቸ የተናሳ  አራተኛ መንግስት ይባላሉ ይህ የሚሆነው ደግሞ ያለ ምንም ተጸኖ ስራቸውን መስራት ሲችሉ ነው ያለዉ ጋዚጠኛ ጥበቡ በለጠ ፣ህጉ ጋዚጠኞች ከእስር ውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ቢፈቅድላቸውም አሁን ግን  ጋዚጠኞች ከመቼውም ግዜ በላይ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡበት ጊዚ ነው ብሏል ።
 
የአራት ኪሎ ሚዲያ መስራች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ጋዚጠኛ አላዛር ተረፈ  የሙያ አጋሩ የሆነው ጋዚጠኛ ዳዊት በጋሻው በመንግስት ሀይሎች የተያዘዉ ባሕር ዳር ዉስጥ መሆኑን አስታዉቋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የካሚራ እቃዊቻቸውን ባልታወቁ ሰዎች መዘረፋን  በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ አታውቀው የነበሩት «አራት ኪሎዎች»  ስራቸውን ከጀመሩ  ጊዚ ጀምሮ መረጃን ለ ህዝብ በማቅረብ ተመራጭ እየሆኑ መምጣት ጀምረው ነበር ።ጋዜጠኛ ዳዊት ትላንት በፊዲራል የመጀመሪያ ፈርድ ቤት አራዳ ምድብ ይቀርባል ተብሎ ሲጠበቅ  የነበረ ቢሆንም ግልፅ ባልሆነ ምክንያት   አለመቀረቡ ታውቆዋል 

ሐና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW