1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛዎች ፈተና በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2016

በጋዜጠኞችና በብዙኃን መገናኛ ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ሕጋዊ ሥርዓትን ብቻ የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን ተጠያቂነት ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል ገልጿል። ጋዜጠኞችን ከሕግ አካሄድ ውጪ ማሰር እየታየ መሆኑን ተገልጿል።

አሳሳቢዉ ጋዜጠኞች እስር
የጋዜጠኞች እስር ምስል Kim Ludbrook/dpa/picture alliance

ጋዜጠኞችን ማሰር የሚዲያ ተቋማትን ማገድ እንዲቆም ተጠየቀ

This browser does not support the audio element.

የጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛዎች ፈተና

በጋዜጠኞችና በብዙኃን መገናኛ ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ሕጋዊ ሥርዓትን ብቻ የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በእነዚህ አካላት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ምክር ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከሕግ አካሄድ ውጪ አሥሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸውና በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱት ጥቆማዎች መገንዘቡን አስታውቋል። ላለፉት አምስት ዓመታት የፍትህ አካሉ የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተደረጉበት ያለ ቢሆንም ጋዜጠኞችንና ተቋማቱን በተመለከተ ተደጋጋሚ የመብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ያለመቻሉ ምክር ቤቱን በእጅጉ እንዳሳሰበው የግለፀው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ችግሩ እንዲፈታ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ጉዳዩን በማሳወቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጥሪ

ፎቶ ማህደር፤ የቀለም ቀንድ ምስል Yekelem Qend

አሳሳቢዉ የጋዜጠኞች እስርና የሃሳብ ነጻነት መደፍለቅ በኢትዮጵያ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው ምክር ቤታችንን አሳስቦታል ያለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አብነቶችን በመጥቀስ እርምት እንዲደረግ ጠይቋል። የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ኃይሉ።

"በኢትዮ ሐበሻ አሳታሚ ድርጅት በየሳምንቱ እየታተመ የሚሰራጨው ጊዮን መጽሔት እና ዋና አዘጋጁ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ከአንድ ሳምንት በኋላ ዋና አዘጋጁ ያለ ክስ ሲለቀቅ መጽሔቱ ከአንድ ወር ከ 15 ቀን በላይ አልተለቀቀም"  ብለዋል።

በተመሳሳይ የትርታ ኤፍ ኤም 97.6 የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን ጳጉሜን 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቱ በጥፀታ ሃይሎች ከተወሰደ በኋላ ከአንድ ወር ከ20 ቀናት በላይ ክስም አልተመሰረተበትም ፣ ፍርድ ቤትም ሊቀርብ አልቻለም ብሏል።ፈተና ያቀጨጨው የኢትዮጵያ ፕረስ

ጋዜጠኞችን አሥሮ የመሰወር ድርጊት አሳሳቢነት

የፀጥታ አካላት ጋዜጠኞችን አስሮ መረጃ መሰብሰብና አስሮ ለቀናት ክስ አለመመስረት እንዲሁም የህትመት ውጤትን ከስርጭት ማገድ  የመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ ስራቸውን  በነጻነት እንዳያከናውኑ የሚያስተጓጉል ተግባር መሆኑን ያስታወሰው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ  የሚኖር ተጠያቂነት በህጉ አግባብ ብቻ መከናወን ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

ላለፉት አምስት ዓመታት የፍትህ አካሉ የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተደረጉበት ያለ ቢሆንም ጋዜጠኞችንና ተቋማቱን በተመለከተ ተደጋጋሚ የመብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ያለመቻሉ ምክር ቤቱን በእጅጉ እንዳሳሰበው የግል ለፀው ምክር ቤቱ ችግሩ እንዲፈታም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ጉዳዩን በማሳወቅ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ባመግለጫው ጠቅሷል።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንን ይዞታ የቃኘው ውይይት

የፕሬስ ነጻነት ምልክት ምስል Michele Cattani/AFP via Getty Images

የጋዜጠኞች እሥር፣ ስደት እና ከሙያቸው የመራቅ እውነታ

ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል በአማራ ክልል ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚሠሩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ታይቷል። ይህ ድርጊት እንዲቆም በያገባናል ባዮች የሚሰጡ መግለጫዎች፣ ውትወታዎች ውጤት ሲያመጡም አልታየም።

አምስት ያህል ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን በየፊናቸው ማስታወቃቸው የቅርብ ጊዜ ዜና ነው።

በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ ኢንተርኔትን በመጠቀም የራሳቸውን የበይነ መረብ የመገናኛ ዐውታር እያቋቋሙ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጥቂት የማይባል ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች እና ንቁ የፖለቲካ ጉዳይ ተሳታፊዎች ጽ/ቤቶቻቸው በተደጋጋሚ እየተሰበረ ንብረቶቻቸው ተዘርፈውባቸዋል ፣ በእሥር እና በሌላም ምክንያት ከጀመሩት ሥራቸው ሲርቁ ተስተውሏል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW