1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛ ባለሙያዎች እሥር

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል በአማራ ክልል ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚሠሩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ታይቷል።

የሲፒጄ ሎጎ
ሲፒጄ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል

የጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛ ባለሙያዎች እሥር

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለሳምንታት ያለምንም ማብራሪያ በእሥር ላይ ይገኛል ያለውን ኢትዮ ኒውስ የተባለውን የበይነ መረብ መገናኛ ዐውታር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ከሰሞኑ ጠይቋል።

ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ እና ለእሥር ሊዳርገው የሚችል ምንም የሙያ ጥሰት የታየበት ሥራ አለማከናወኑን ባልደረባው ለዶቼ ቬለ ተናግሯል።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰው እሥር እና እንግልት እንዲቆምም ጠይቋል።

የጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛዎች ፈተና በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የሕትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው እንዳሳሰበው ከዚህ በፊት የጠየቀው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እርምት እንዲደረግ መጠየቁ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ ስላለው የጋዜጠኞች የሥራ ነፃነት እና ድባብ የጠየቅናቸው ሁለት ጋዜጠኞች መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈጥረው ጫና ቀጥተኛ ተጠቂ በመሆናቸው የጋዜጠኝነት ሥራን መሥራት የሚያስችል ዐውድ እንደሌለና ይልቁንም ብዙዎች ለእሥር እና ሥደት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

የጋዜጠኞች የመታሰር ፣ የመፈታት ሁኔታ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ሲይዙ የመሻሻል አዝማሚያ ያሳየው የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ተመልሶ ሥጋት ውስጥ ወድቋል። ምስል AFP/E. Soteras

ኢትዮጵያ ውስጥ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው ፣ መያዛቸው ፣ መለቀቃቸውና ዳግም መታሰራቸው ተደጋግሞ ታይቷል።

በተለይ የበይነ መረብን በመጠቀም በፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚተነትኑ ፣ ዘገባዎችን የሚሠሩ ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች በደረሰባቸው ማስፈራራት፣ ቢሮ ተሰብሮ ዘረፋ ፣ ዛቻ እና መሰል ጉዳዮች ወይ ከሙያው ርቀዋል፣ ወይ ታሥረዋል አልያም ሀገር ጥለው ተሰደዋል።
የኢትዮ ኒውስ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ በፖሊስ በቅርቡ ከተያዙ ጋዜጠኞች አንደኛው ነው። ባልደረባው በለጠ ካሳ እንደሚለው በላይ ሊታሰር የሚችልበት የምለው የሰራው ዘገባ የለም ።

የጋዜጠኞች ስደት፣ ከሙያቸው የመራቅ ፈተና

ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል በአማራ ክልል ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚሠሩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ታይቷል። ይህ ድርጊት እንዲቆም በያገባናል ባዮች የሚሰጡ መግለጫዎች፣ ውትወታዎች ውጤት ሲያመጡም አልታየም። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አሁን ያለው የዘርፉ እውነታ ፈታኝ መሆኑን ጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን የፈተነው የመረጃ እጦት

በቅርቡ አምስት ያህል ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን አስታውቀው ነበር። የኢትዮ ኒውስ ዋና አዘጋጅ በለጠ ካሳ በባልደረባውም ይሁን በሌሎች የሙያው ሰዎች ላይ የሚደርሰው እንግልት ለዚህ ችግር መነሻ መሆኑን ይጠቅሳል። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ እየደረሱ ያሉ ተመሳሳይ ችግሮችን የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲፈቱ ጠይቋል

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW