የግሪክና የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ዉዝግብ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2007ማስታወቂያ
ባለፈዉ እሁድ በግሪክ የተካሄደዉ የአበዳሪ ድርጅቶችን ቅድመ ሁኔታ የመቀበል ያለመቀበል ሕዝበ ዉሳኔ ከስልሳ ከመቶ በላይ የሚሆነዉ የግሪክ ሕዝብ ቅድመ ሁኔታዉን መቃወሙ ከታወቀ በኋላ በግሪክ፤ በአበዳሪዎቿና በዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት መካከል ያለዉ ግንኙነት አጣብቂኝ ዉስጥ በመግባቱ ነበር ስብሰባዉ የተጠራዉ። በአሁኑ ወቅት ግሪክ ዉስጥ ባንኮች ተዘግተዋል። የኤኮኖሚ እንቅስቃሴዉም ቆሟል። ይህ ችግሯ ባፋጣኝ ካልተፈታም ግሪክ ከዩሮ ልትወጣ ልትገደድ፤ ሕዝቡም ለከፋ ችግር ሊጋለጥ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ