1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የግራ እና ቀኝ ትግል እና የኢትዮጵያ መጻኢ ዕጣ ፈንታ

እሑድ፣ ሰኔ 15 2017

ኢትዮጵያ ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ልታደርግ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። በሀገሪቱ በተለይ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል። የተለያየ አላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ የመቆም አዝማሚያ አይታይም።

Äthiopien Sitzung des Nationalen Wahlausschusses von Äthiopien (NEBE) zum Gesetzesentwurf
ምስል፦ Solomon Muche/DW

ከተለጠጠው ትግል ባሻገር የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሁን?

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ልታደርግ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። በሀገሪቱ በተለይ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል። የተለያየ አላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ የመቆም አዝማሚያ አይታይም። በሌላ በኩል የምርጫ ጊዜ ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ በፌዴራል እና በክልል ደረጃ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣዩ ምርጫ የገዢውን ፓርቲ ለመገዳደር ምን ያህል ተዘጋጅተው ይቀርባሉ የሚለው ጥያቄም መነሳቱ አይቀርም።

"ካልቻሉ አሁን ከስልጣን መልቀቅ አለባቸው" ተቃዋሚዎች

በቅርቡ የታጣቂ ቡድን ተወካዮችን ጨምሮ የተለያዩ አመለካከቶች የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ አክቲቪስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች የተሳተፉበት አንድ የኦን ላይን የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መንግስታዊ የስረዓት ለውጥ እንዲመጣ ልዩነታቸውን ወደ ጎን አድርገው በጋራ ለመስራት መክረዋል። ምንም እንኳ ተሳታፊዎቹ በጣም የሰፋ የፖለቲካ ዓላማ እና ግብ እንደምን ሃሳባቸውን ሊያሳካው ይችላል የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ ባይቀርም።

እንወያይ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ፋይዳዉ ምን ይሆን?

ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስታዊ ስረዓቱን ለማስወገድ የተለያዩ አላማዎች ሰንቀው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ዓላማቸውን በኃይል ማሳካት ቀላል እንደማይሆን ይነገራል። በሌላ በኩል ደግሞ በሰለማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ በያዙት መንገድ በነጻነት ለመንቀሳቀስ ገዢውን ፓርቲ ለመገዳደር የዴሞክራሲ ምህዳሩ እንደጠበባቸው ሲገልጹ ይሰማሉ ። ለዚህም ሲፈጸሙባቸው የነበሩ የፓርቲ መሪዎች እስራት እና ወከባ ፣ የቢሮ መዘጋት እና አባላትን የማሰደድ ተግባራት በአስረጂነት ያቀርባሉ ።

የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው

ይህንኑ ተከትሎ ኢትዮጵያ አሁን ለትጥቅም ሆነ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምቹ እንዳልሆነች እየተነገረ ባለበት ሰዓት ነው እንግዲህ ሀገራዊዉን ምርጫ ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ያለችው ።

ከትጥቅ ትግል እና  ጠቧል የሚል ክስ ከሚቀርብበት የዴሞክራሲ ምህዳር ባሻገር የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ? የሳምንቱ የእንወያይ ዝግጅታችን ርዕስ ነው።

በውይይቱ ላይ ዶ/ር ነገራ ጉደታ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ተመራማሪ

አቶ ገብረመድህን ገብረሚካኤል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ  የሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች መምህር ናቸው።

አቶ ሲሳይ አሰምሬ ከአዲስ አበባ ተሳታፊዎች ናቸው 

አወያዩ ታምራት ዲንሳ ነው

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW