1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአስመራ የግብጽ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች የሦስትዮሽ ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥቅምት 1 2017

አስመራ በትናንትናው ዕለት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼይክ ሞሃሙድ፤ የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲና የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የተሳተፉበትን አፈወርቂ የተሳተፉበትን የሦስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ አስተናግዳለች።

 በርበራ ወደብ
በርበራ ወደብ ፎቶ ከማኅደርምስል Eshete Bekele/DW

የግብጽ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች ጉባኤ

This browser does not support the audio element.

 ጉባኤው የተጠራውና የተስተናገደው በፕሬዝዳንት ኢሣይያስ ሲሆን፤ የየሦስቱም አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የደህንነት ሀላፊዎችም በስብሰባው መሳተፋችው ተገልጿል።

መሪዎቹ የመሰረቱት ጥምረትና የተስማሙባቸ ጉዳዮች

መሪዎቹ በሁለትዮሽ፤ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በጥልቀት በመወያየት በሦስቱ አገሮች መካከል ያለውን ወዳጀነትና ትብብር ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለማጠናከርና ለማሳደግ መስማማታቸው ተገልጿል። ሦስቱ መሪዎች ከጉባኤው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግልጫ፤ ኤርትራና ግብጽ ለሶማሊያ ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የሦስቱን አገሮች ስልታዊ ትብብርን የሚያሳልጥ ከፍተኛና የሦስቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚስተፉበት ኮሚቴም የሚቋቋም መሆኑም ተገልጿል።

ለሶማሊያ ሊሰጡ የታሰቡ ድጋፎችና እርዳታዎች

መሪዎቹ በሰብሰባቸውና በጋራ መግለጫቸው፤ የአገሮች ሉአላዊነት፣ ነጻነትና የግዛት አንድነት መከበርን አስፈላጊነት አጽንኦት የሰጡበት እንድነበርም ታውቋል። በተጨማሪም የሶማሊያን ተቋማት ለማጠናከርና ከውስጥና ከውጭ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች እንድትቋቋም፤ ሦስቱ አገሮች አንድነታቸውን በማጠናከር እንደሚሰሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።፡ ግብጽ በሶማሊያ በሚሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል ለመሳተፍ መወሰኗንም መሪዎቹ ያደነቁ መሆኑ ተገልጿል። በሶማሊያ ስለሚሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል ግን ባለድርሻ አካላቱ በርካታ እንደሆኑና በተለይ አልሸባብን በመዋጋትና በመግታት በኩል የኢትዮጵያ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ወታደሮች አስወጥቶ በግብጽ ለመተካት የሚደረገው ጥረት ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ እንደሚገጥመው ነው የሚታመነው።

የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድምስል REUTERS

 የሶማሊያና ኢትዮጵያ ቅራኔና የኤርትራና ግብጽ ክሶማሊያ ጎን የመቆም እንዴትነት

የግብጽ ሶማሊያና ኤርትራ ወዳጃነት በዚህ ደረጃና ፍጥነት ያደገው ግን ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ክምትቆጥረው ሶማሊላንድ ጋር የወደብ አግልግሎትን በሚመለክት የመግባቢያ ስነድ ከተፈራረመች በኋላ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ሶማሊያ ግዛቲቱን የራሷ ግዛት አካል አድርጋ ስለምትቆጥር፤ የኢትዮጵያን እርምጃ የአገሪቱን ሉላዊነት የሚጥስ አድርጋ ወስዳዋለች። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንንኙ ከማቋረጥ አልፎ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ዘመቻም በማካሄድ ላይ ነች። ግብጽም ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ባላት የቆየ እሰጥ አገባ አሁን በኢትዮጵያና ሶማሊያ ውዝግብ ጣልቃ ብትገባና ከሶማሊያ ጎን ብትቆም የሚያስደንቅ አይደለም ነው የሚባለው። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ከፕሪቶሪይው ስምምነት በኋላ ኤርትራ ከጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ መንግሥት ጋር ያላት ግንኙነት መሻከሩ ሲነገር ቢቆይም፤ በዚህ ደረጃ ከሶማሊያና ግብጽ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ በተቃራኒ ትቆማለች ተብሎ የሚታሰብ እንዳልነበር ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። ያም ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩና ስለማዊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ትናንት በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ተስምተዋል።

ይህ አስመራ ላይ የተደረገው የሦስቱ አገሮች ጉባኤና የተሰመሰረተው አንድነት ግን በኢትዮጵያና በሶማሊያ ለው አለመግባባት እንዲሰፋና አካባቢውንም ወደ ቀውስ እንዲያመራ ከሚያድርግ በስተቀር ሦስቱም አገሮች በየበኩላቸው አሉን የሚሏቸውን ጥቅሞች እንኳ ለማስጠበቅ እንደማይረዳ ነው ተንታንኞች የሚናገሩት። የምሥራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ራሺድ አብዲ በወትሮው የቲዊተር በአሁኑ የኤክስ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፤ «አስመራ ላይ የታየው የሦስቱ አገሮች ጥምረት በዋናነት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው ስምምነት መሰረት የናቫል ቤዝ (የባሕር ኃይል የጦር ሰፈር) እና ወደብ እንድታገኝ ለማድረግ ያለመ ነው»።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW