የግብፅ ወቅታዊ ሁኔታ
ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2005ማስታወቂያ
ካይሮ ዉስጥ ሃምሳ አባላትን ያካተተ አንድ የሕገ-መንግስት አርቃቂ ምክር ቤት መቋቋሙና፤ በስድሳ ቀናት ዉስጥ አዲስ የሕገ-መንግስት ረቂቅ እንደሚቀርብ ተነግሮአል። የሕገ-መንግስት አርቃቂዉ ምክር ቤት ሊቀመንበር የቀድሞዉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እጩ የነበሩት አምር ሙሳ መሆናቸዉ ተመልክቷል። በሌላ በኩል 50 አባልትን ባቀፈዉ በእዚህ የሕገ-መንግስት አርቃቂ ምክር ቤት ዉስጥ፤ በቂ ተወካዮች አልተካተቱበትም ሲሉ ሙስሊም ወንድማማቾች ይወቅሳሉ። የሳውዳረቢያው ዘጋቢያችን ነብዩ ሲራክ አጭር ዘገባ አድርሶናል።
ነብዩ ሲራክ
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ