1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ዉዝግብ የአረቡ ዓለምና አዉሮጳ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 2 2005

የግብፅ የአስቸኳይ ሁኔታ አገልግሎት ኀላፊ ሙሐመድ ሱልጣን እንዳስታወቁት ቁጥራቸው ከ51 የማያንስ ሰዎች ሲገደሉ፤ 435 ቆስለዋል። የአዉሮጳ ኅብረት ድርጊቱን አዉግዟል።

ምስል Reuters

ጦር ኃይሉ ግድያውን የፈጸሙት «አሸባሪዎች» ናቸው ሲል፤ የዐይን ምሥክሮች፤ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር ደጋፊዎች ጭምር፤ ፀጥታ አስከባሪዎች የማስጠነቀቂያ ተኩስ ወደ ሰማይ ሲተኩሱና ሚያስለቅስ ጋዝ ሲረጩ፤ «ወንጀለኞች» ያሏቸው፣ የሲብል ልብስ የለበሱ ሰዎች ግድያውን መፈጸማቸውን ገልጸዋል። ግድያው ዓለም አቀፍ ውግዘት ተሰንዝሮበታል። የግብጽን ወቅታዊ ውዝግብ በተመለከተ በዐረቡ ዓለም ፤ በተለይ በስዑዲና በዐረቡ ባህረ ሰላጤ፣ መገናኛ ብዙኀን የሚያቀርቡት ምን ይመስላል? የህዝቡስ አስተያየት? የጂዳውን ዘጋቢአችንን ፣ ኒቢዩ ሲራክን ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮት ነበር።

ምስል Getty Images

ትናንት ግብጽ ዉስጥ በጦር ኃይሉና ስልጣናቸዉን እንዲለቁ በተገደዱት የፕሬዝደንት ሞሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች መካከል በነበረዉ ግጭት ከሃምሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉና በመቶዎች የሚቆጠሩት መቁሰላቸዉን የአዉሮጳ ኅብረት አዉግዟል። የኅብረቱ ቃል አቀባይ ለግብጽ መረጋጋት እያንዳንዱ ወገን ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዘቡ ሲሆን ኅብረቱ ለግብጽ የሚሰጠዉን ርዳታ ለጊዜዉ እንደማያቆም ሆኖም ግን ሁኔታዉን እንደሚያጠና አመልክተዋል። የተከፋፈለዉን የኅብጽ ህዝብ ወደሰላም ለማምጣትም ኅብረቱ ከግብጽ ፖለቲካ ኃይሎች ከሁሉም ወገኖች ጋ መነጋገሩን እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። በአሁኑ ይዞታ ግን ለተወገዱትም ሆነ አሁን ለተሰየሙት ፕሬዝደንቶች የአዉሮጳ ኅብረት እዉቅና እንደማይሰጥ ተነግሯል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከአዉሮጳ ኅብረት የተከታተለዉን እንዲያጋራን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነብዩ ሲራክ/ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW