1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ፖለቲካዊ ዉዝግብና ሥጋቱ

ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2005

የግብፅ ጦር ኃይል እንደዛተው ፕሬዝዳንት ሙርሲን ከሥልጣን አስወግዶ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል ። ጦር ኃይሉ የግብፅን ህገ መንግሥት በማገድ አዲስ ምርጫ እንደሚጠራና እስከዚያውም ጊዜያዊ መንግሥት እንደሚያቋቁም አስታውቋል ።

Bildnummer: 59172329 Datum: 30.01.2013 Copyright: imago/Sven Simon Präsident Mohammed MURSI Pressegespräch beim Staatsbesuch des ägyptischen Präsidenten im Bundeskanzleramt in Berlin, Deutschland am 30.01.2013. People Politik xmk x0x 2013 quer Politik PL politisch Politiker Staatsgast Besuch Gast Ägypten ägyptischer Staatspräsident Präsident aktuellPolitik Aktion Action Einzelbild Freisteller halbe Figur single shot Datenbank Mohamed 59172329 Date 30 01 2013 Copyright Imago Sven Simon President Mohammed Mursi Press interview the State Visit the Egyptian President in Federal Chancellery in Berlin Germany at 30 01 2013 Celebrities politics xmk x0x 2013 horizontal politics PL politically Politicians State Guest Visit Guest Egypt Egyptian State President President aktuellPolitik Action shot Action Single cut out Halbe Figure Single Shot Database Mohamed
ፕሬዝዳንት ሙርሲምስል Imago

የግብፅ መንግሥትና ተቃዋሚዎቹ የገጠሙትን ደም አፋሳሽ ፖለቲካዊ ዉዝግብ በድርድር እንዲፈቱ የሐሪቱ ጦር ሐይል የሠጠዉ የአርባ-ሥምንት ሠዓታት ገደብ ከአንድ ዓት በፊት አብቅቷል።ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ሥልጣን እንዲለቁ ተቃዋሚዎቻቸዉ በአደባባይ ሠልፍ የሚያደርጉባቸዉን ግፊትም ሆነ የጦሩን ማስጠንቀቂያ አልተቀበሉትም።የሙርሲ እና የተቃዋሚዎቻቸዉ ደጋፊዎች በአደባባይ የገጠሙት ግጭትና ረብሻ እንደቀጠለ ነዉ።በሁለቱ ወገኖች መካካል ትናንት ሌሊቱን ብቻ በተደረገ ግጭት አስራ-ስድስት ሰዉ ተገድሏል።ጦሩ የሠጠዉ ሠዓተ-ገደብ ቃበቃ በሕዋላ የሚወስደዉ እርምጃ ምንነት ዛሬም ሲያነጋግር ነዉ የዋለዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።


መከላከያ ሚንስትርና የጦር ሐይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታሕ ኻሊል አል-ሲ ሲ፥ እንደ ገማል አብድናስር በቀጥታ መፈንቅለ መንግሥት፥ ወይም እንደ ማርሻል መሐመድ ሁሴይን ታንታዊ በተዘዋዋሪ፥ የካይሮ ቤተ-መንግሥትን ለመቆጣጠር ማቀድ-አለማቀዳቸዉ በርግጥ አለየም።ጦራቸዉ ጣልቃ-ለመግባት መወሰኑን ግን ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲና ደጋፊዎቻቸዉ በቀጥታ ሲቃወሙት ሙርሲን የሚቃወሙት ሐይላት በመደገፍና-በመቃወም መሐል ለሁለት እንደተከፈሉ ነዉ።

«ይሕ፥ ፕሬዝዳንት ሙርሲ፥ ደጋፊዎቻቸዉና መንግሥታቸዉ ሐገሪቱን ለመምራት ብቃት እንደሌላቸዉ የሚያሳይ ነዉ።በሙርሲ ላይ ከባድ ጫና ለማሳረፍ ጦር ሐይሉ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ጥሩ ነዉ።»

ሌላዉ-የሙርሲ ተቃዋሚ አከለበት።

«ያለን ብቸኛ አማራጭ ጦሩ ሁሉንም ጉዳይ ፖለቲካዉን በሙሉ እንዲቆጣጠረዉ ነዉ።ከዚያ ምርጫ ይደረጋል።ምናልባት ባንድ ዓመት ጊዜ።»

እሱም የሙርሲ ተቃዋሚ ነዉ።ሥለ ጦሩ ጣልቃ-መግባት ግን፥ እንደሱዉ ሙርሲን የሚቃወሙትን ይቃወማል።

«እኔ የጦር ሐይሉ ይመራዉ የነበረዉን ጊዚያዊ ወታደራዊ መንግሥት ከሚቃወሙት አንዱ ነበርኩ።አሁንም የጦር ሐይሉ ሥልጣን መያዙን እቃወማለሁ።አንድም ቀን በወታደራዊ ሐይል መገዛት አልፈልግም»
የፈርዖኖቹ ሥልጡን፥ ጠንካራ፥ ጥንታዊት ሐገር ጠንካራ ፈርዖን አጥታ፥ሁሉም ፈርዖን ሊሆንባት እየተሻማ፥ እየተወዛገበ፥ እየተላተመ፥ ገድሎ ይሞትባት፥ ጥሎ ይወድቅባት ይዟል።የከንግዲሕ ጉዞዋ እንዴት፥ ወዴትነት ለፖለቲካ ተንታኞች ግምት ሲበዛ ከባድ-ግራ አጋቢ፥ አስጊም ነዉ።የርስ በርስ ጦርነት ሥጋት።

የቀድሞዉ የረጅም ጊዜ አምባገነን ገዢ መሐመድ ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣን ለማስወገድ ከሙባራክ ታማኞች ታንክ፥ መትረየስ ጋር ባንድ አብሮ የተጋፈጠዉ፥ የሕዝባዊ፥ ሠላማዊ ትግል አብነት፥ የዲሞክራሲ፥ የፍትሕ እኩልነት ተስፋ የነበረዉ ግብፃዊ ዛሬ እብዙ ሥፍራ-ተከፍሎ እሰወስት የሚከፈሉ ዋና ዋና ሐይላት እየነዱት ነዉ።ጉዞዉ ወደ ጥፋት ይሁን ወደ ልማት ግን አለየም።

ግብፅ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስተናገደችዉ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈዉ የዛሬ ዓመት ይሕን ጊዜ ሥልጣን የያዙት ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲ እና የቀድሞ የፖለቲካ ፓርቲያቸዉ ሙስሊም ወንድማማቾች አንደኛዉን ጎራ ይመራሉ።

«ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሠረት የላቸዉም።ሁኔታዉን በግልፅ ለመወሰን ከፈለጉ ሙርሲ የተመረጡበት የአራት-ዓመት ዘመነ-ሥልጣን እስኪያበቃ መጠበቅ አለባቸዉ።»

በአምናዉ ምርጫ የተሸነፉት ተቃዋሚዎች፥ የሙባረክ ዘመን ባለሥልጣናት፥ በፕሬዝዳት ሙርሲ አመራር ያልረኩ ወገኖች ለጊዜዉ አንድ የሚመስል ግንባር ፈጥረዉ-ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን ይልቀቁ ይላሉ።ሰወስተኛዉ፥ ሁለቱ ወገኖች በየፊናቸዉ በየአደባባዩ የሚያሰልፉት ሕዝብ እስኪጋጭ፥ እስኪደባደብ፥ እሲኪጋደል፥ ጠብቆ ብቅ አለ።ጦር ሐይሉ።ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን እንዲፈቱ የሠጠዉን ሠዓተ-ገደብ ግን መሐመድ ሙርሲና ደጋፊዎቻቸዉ አልተቀበሉትም።

«ማንም ሠዉ እነሱ በሚሉት መንገድም ሆነ በሐይል፥ በሕገ-መንግሥቱ ጣልቃ የመግባት ሥልጣን የለዉም።ማንም የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የመቀየር ወይም አዲስ ሥርዓት የመመሥረት ሥልጣን የለዉም።»

አሉ ፕሬዝዳቱ ትናንት።ሙርሲ በቴሌቪዥን ሲነጋሩ ደጋፊ-ተቃዋሚዎቻቸዉ እዚያዉ ካይሮ ዉስጥ ይገዳደሉ ነበር።ጄኔራል ሲሲ የቆረጡት ገደበ-ሠዓትም አብቅቷል።እና ታንክ መትረየስ አስጠምደዉ ካይሮ ቤተ-መንግሥት ቢገቡስ? «ምርጫዬ» አሉ ሙርሲ «ሞት»

ፕሬዝዳንቱና ጄኔራሉ በደሕናዉ ጊዜምስል picture-alliance/dpa
ተቃዉሞዉምስል Reuters
ጄኔራል ሲሲምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ




ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW