የግድያ፣ የእገታ እና የዝርፊያ ስጋት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 26 2015ማስታወቂያ
በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በታጣቂ ኃይሎች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል። ባለፈው ሳምንትም በጉራጌ ዞን መረቆ እና መስቃን ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል። በዚሁ ዞን አንድ አሽከርካሪ 50 ብር ባለመስጠቱ በፖሊስ መገደሉም ተሰምቷል። በአሽከርካሪዎች እና በመንገደኞች ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ እገታ እና ዝርፊያም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከዚህም እዚያም ይሰማል። ያለፈው ሰኞም ከባሕር ዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 63 ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰምቷል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታየው የደህንነት ዋስትና ስጋት እንዴት ይገለጻል? መንግሥትስ ኃላፊነቱን ተወጥቷል ማለት ይቻል ይሆን? በየአካባቢያችሁስ ምን ታዘባችሁ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን።
ፀሐይ ጫኔ
ነጋሽ መሐመድ