የጎርፍ አደጋ ያጠቃው አፋር
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2012![Äthiopien | schwere Überschwemmung in Afar](https://static.dw.com/image/54495556_800.webp)
ማስታወቂያ
በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ከተፈጥሯዊ ፍሰቱ ሰብሮ በመውጣት በየዓመቱ የሚያደርሰው ጥፋት በዘላቂነት መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ተጠቆመ። ከሰሞኑ በዚሁ መዘዝ ከ67 ሺህ በላይ በጎርፉ ሲጎዳ ከ27 ሺህ የሚበልጥ ሕዝብ መፈናቀሉ ተሰምቷል። በጎርፉ ለተጎዱት የዕለት ደራሽ ዕርዳታዎች እየተደረጉ ቢሆንም ከተጎጂዎች ብዛት አኳያ በቂ እንዳልሆነ የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ለዶቼ ቬለ አመልክቷል። በተፋሰሱ ላይ ጎርፍ እንዳይመጣ የሚሠሩ ሥራዎች በፌደራል መንግሥት በኩል ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ አጠናቅሯል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ