1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎንደር ከተማ ወቅታዊ ሁኔታና የከተማዋ የአስቸኳ ጊዜ እዝ መግለጫ

ሰኞ፣ መስከረም 14 2016

ፋኖ በጎንደር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመክፈት ያደረገውን ሙከራ “አከሸፍኩ” ሲል የጎንደር ከተማ የአስቸኳ ጊዜ እዝ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ ነዋሪዎች ዛሬ አልፎ አልፎ ተኩስ ቢሰማም የማህበራዊ አገልግሎቶች በከተማዋ ባይኖሩም መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

ጎንደር ከተማ
ጎንደር ከተማምስል Alemnew Mekonnen/DW

“ ትናንት ከፍተኛ ውጊያ ነበር ዛሬ ግን የተሸለ እንቅስቃሴ አለ፣ ሆኖም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ ይሰማል” ተብሏል

This browser does not support the audio element.


ፋኖ በጎንደር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመክፈት ያደረገውን ሙከራ “አከሸፍኩ” ሲል የጎንደር ከተማ የአስቸኳ ጊዜ እዝ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ ነዋሪዎች ዛሬ አልፎ አልፎ ተኩስ ቢሰማም የማህበራዊ አገልግሎቶች በከተማዋ ባይኖሩም መጠነኛ መረጋጋት በከተማዋ ተናግረዋል፡፡ 
የጎንደር ከተማ የአአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ ጣቢያ ትናንት ባወጣው መግለጫ “ጠላት” ብሎ የጠራው ኃይል ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት “ወደ ጎንደር ከተማ ሰርጎ በመግባት በስም ባልተጠቀሰ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሯል ብሏል፡፡ መግለጫው አክሎም የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ማክሸፋቻን አመልክቷል፡፡ብርቱ ዉጊያ በጎንደር

ከሀምሳ በላይ የሚሆኑ የቡድኑን አባላት ማቁሰሉንንና መግደሉን ያመለከተው መግለጫው፣ “ቀሪው ኃይል ደግሞ ተበትኗል” ሲል የከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ ጣቢያ ገልጧል፡፡ ቡድኑ “ጎደርን ተቆጣጥረናል እያለ የሚያሰራጨው ዘገባም ከእውነት የራቀ ነው ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡ 
ትናንት የነበረውን ውጊያና የዛሬውን የጎንደር የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ከጎንደር ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹን ጠይቀን ነበር፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ ከነገሩን ነዋሪዎች መካከል አንዷ እንዲህ ብለዋል፡፡ 
“ ትናንት ከፍተኛ ውጊያ ነበር ዛሬ ግን የተሸለ እንቅስቃሴ አለ፣ ሆኖም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ ይሰማል” ብለዋል፡፡ ሌላ የጎንደር ከተማ አስተያየት ሰጪም ዛሬ ጠዋት ለተወሰነ ጊዜ ቀበሌ 18 ወይም “ደሳለኝ” በሚባለው የከተማው ክፍል የተኩስ ድምፅ እንደነበር ጠቁመው አሁን ከተማዋ በመንግስት ኃይሎች ቁጠጥጥር ስር እንደሆነች ገልፀዋል፣ በድንጋይ ተዘግተው የነበሩ መንገዶችም ተከፍተዋል ነው ያሉት፡፡ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ማዕከላዊ ጎንደር ምስል Alemnew Mekonnen/DW

 ከጎንደር ሆስፒታል ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው አንድ የጎንደር ከተማ እንደገለጹልን ለህክምና ወደ ሆስፒታል የመጡ የፋኖ ቁስለኞችን የፀጥታ ኃይሎች ወስደዋቸዋል፡፡ ለህክምና ወደ ጎንደር ከተማ የመጡ ቁስለኞችን የፀጥታ ኃይሎች መውሰዳቸውን ከጓደኞቻቸው እንደሰሙ ደግሞ አንድ የጎንደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ ነግረውናል፡፡ 
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በሆስፒታሉ 4 ያህል ቁስለኞችን እንደተመለከቱ የህክምና ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ ከክልሉመንግስት የሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት ስልክ ሊነሳ ባለመቻሉ አልተሳካም፡፡

ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ 
ዮሃንስ ገብረግዚአብሄር 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW