1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና

ሰኞ፣ ሐምሌ 14 2017

ፓርኩ የራሱ የሆኑ ጠባቂዎች ቢኖሩትም አጠቃላይ የብሔራዊ ፓርኩን ይዞታ መቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታ እንደሌለ ያስረዱን ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ዋለ ናቸው፡፡

የሰሜን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክ (ከማኅደራችን)
የሰሜን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክ (ከማኅደራችን)ምስል፦ Sololomon Muchie/DW

የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሚገኘው የጎደቤብሔራዊ ፓርክ ለግጦሽና ለህገወጥ እርሻም እየተጋለጠ እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ባለው  የፀጥታ ችግር ምክንያት የፓርኩን አሁናዊ ይዞታ ማወቅ እንዳልተቻለም የፓርኩ ኃላፊ አመልክተዋል። 
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማና በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች መካክል ላይ የሚገኘው የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ ባለው የፀጥታ ችግር አሁን ያለበትን ሁኔታ በአግባቡ መቃኘትና ችግሮቹን ማወቅ እንዳልተቻለ  የፓርኩ  ኃላፊ አቶ ይርጋ ታከለ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ተናግረዋል፡፡ በፓርኩ ህገወጥ ግጦሽ፣ ህገወጥ እርሻና ህገወጥ አደንም እንድሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

“ፓርኩ የራሱ የጥበቃ ኃይል ቢኖረውም አሁን ባለው ሁኔታ በቂ አይደሉም” የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት

ፓርኩ የራሱ የሆኑ ጠባቂዎችቢኖሩትም  አጠቃላይ የብሔራዊ ፓርኩን ይዞታ መቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታ እንደሌለ ያስረዱን ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ዋለ ናቸው፡፡ በፓርኩ አንደኛው ክፍል ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ዘልቆ መሄድ የማይቻልበት ሁኔታ መኖሩን አመልክተዋል፡፡

“የፓርኩን ችግር ለምፍታት በጋራ ይሰራል” የወረዳው አስተዳደር

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቱ ስመኘው የፓርኩን ችግሮች ለመፍታትና ወደ ቀድሞው ይዞታው ለመመለስ አዋሳኝ ከሆነው ከመተማ ወረዳ ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ነግረውናል፡፡
ጽ/ቤቱን በወረዳው ማዕከል አብርሀ ጂራ ያደረገው የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ ይርጋ ታከለበህገውጥ መንገድ ወደ ፓርኩ የገቡ አካላትን በሀገር ሽማግሌዎችና በሐይማኖት አባቶች ምክር ጭምር ከፓርኩ እንዲወጡ የማድረግ ሥራም እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የጎደቤ ብሄራዊ ፓርክ የተለያዩ ብርቅየ አእዋፋትና እንስሳትን በውሰጡ አቅፎ የያዘ ፓርክ ነው፡፡
የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ 18ሺህ 691 ሄክታር ስፋት ሲኖረው፣ ለ5 ዓመታት በጥብቅ ደንነት ከቆየ በኋላ ከ2009 ዓም ጀምሮ በአማራ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ ፓርክ ሆኖ መቋቋሙን ከፓርኩ ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW